ጤነኛ

በኤች አይቪ የታመሙ ሴሎችን የሚገለው ተስፋ ሰጪ የኤች አይቪ መድሃኒት

የመድሃኒቱ ሙከራ ሰዎች ላይ የተደረገ ሲሆን በሙከራው የተሳተፉ የቫይረሱ ተጠቂዎች ላይ ቫይረሱ በ99 ፐርሰንት ያህል ሲቀንስ ተስተውሏል።

በካሊፎርኒያ በሚገኘው ፖሊፔፕታይድ ላብ የተፈበረከው ጋሞራ የተባለው መድሃኒት በኤች አይቪ የተጠቁ ሴሎች ጋር በመዋሃድ እራሳቸውን እንድያጠፉ ያደርጋል።

በሰው ላይ ሙከራ ያካሄደው ዛዮን ላብ እንደሚናገረው መድሃኒቱ ከውጤታማነቱ በተጨማሪ ጤና ላይ ችግር የማይፈጥር መሆኑን በአጥጋቢ ደረጃ አሳይቷል። ዛዮን ላብ በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት ወራት ሙከራቸውን በማስፋት 50 ሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ ያቅዳሉ።

felixioncool / Pixabay

የአሁኑ ሙከራ የተከናወነው ኡጋንዳ የሚገኘው ዶክተር ሮናልድ ሜሞሪያል ሆስፒታል ሲሆን 9 ኤች አይቪ ፖዘቲቭ ታካሚዎች በሙከራው ተሳትፈዋል። ሙከራውን ተከትሎ ቫይረሱ በታካሚዎቹ ሰውነት 90 ፐርሰንት ያህል ቀንሶ ታይቷል። ይህን ውጤት ተከትሎ ታካሚዎቹ ለ5ሳምንት ተጨማሪ የጸረ ቫይረስ ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን ቫይረሱ ከሰውነታቸው በ99ፐርሰንት ያህል ቀንሶ ታይቷል። ታካሚዎቹ የ94 ፐርሰንት የሲዲ4 ጭማሪ አሳይተዋል።

የዛዮን ሜዲካል ስራስኪያጅ ኤስሚራ ናፍታሊ እንደሚያስረዳው አንዳንድ የጸረ ቫይረስ ህክምናዎች ኤችአይቪ ቫይረስ በምርመራ ማግኘት እስኪከብድ ያህል የማጥፋት አቅም ቢኖራቸውም ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከሰውነት አያጠፉትም። ይህ መድሃኒት ግን የቀሩትንም ቫይረሶች የማጥፋት አቅም እንዳለው ይናገራል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ