ጤነኛ

ወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶችን ለረጅም ግዜ መውሰድ በጤና ላይ ችግር ይፈጥራል?

ለረጅም አመታት ያለማቋረጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት የሚወስዱ ሴቶች አሉ። በሰውነት ውስጥ ተቀብሮ በሆርሞኖች አማካኝነት እርግዝናን የሚከላከለውን አይዩዲን(IUD) ለአመታት በመጠቀም እርግዝናን የሚከላከሉ ሴቶች አሉ። እነዚህ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች በጤና ላይ ምን ያህል ችግር ይፈጥራሉ?

የአጭር ግዜ ክፉ ጎኖች(Side effects)

በሰውነት ውስጥ የሆርሞን ለውጥ በማምጣት እርግዝናን የሚከላከሉ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች በሰውነት ላይ የአጭር ግዜ ክፉ ጎን ሊኖራቸው ይችላል። ነገር ግን ሁሉም ሰው ላይ አይፈጠሩም። በዛ ቢባል ለተወሰኑ ወራት ቢቆዩ ነው። የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፦

  • ከወር አበባ ግዜ ውጭ ደም መፍሰስ
  • ራስ ምታት
  • ማቅለሽለሽ
  • የጡት መሳሳት
  • ክብደት መጨመር
  • የጸባይ መዋዠቅ

የረጅም ግዜ ክፉ ጎኖች

ወሊድ መቆጣጠሪያን ለረጅም ግዜ መጠቀም አብዛኛው ሰው ላይ የሚፈጥረው የጤና ችግር የለም። እንደ ናሽናል ካንሰር ኢንስቲቲውት ከሆነ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች የጡት እና የማህጸን ጫፍ ካንሰር ተጋላጭነትን ሊጨምሩ ይችላሉ ብሎ ያስቀምጣል። ነገር ግን የማህጸን ውስጥ ካንሰር፣ የእንቁሊጥ ካንሰር እና የደንዳኔ ካንሰር ተጋላጭነትን ሊቀንሱ ይችላሉ ይላል።

የወሊድ መቆጣጠሪያ ሆርሞኖች አንዳንድ የካንሰር ሴሎች የመፈጠር እድላቸውን ሊጨምሩ ይችላሉ። ሌሎች የካንሰር ሴል አይነቶች ግን እንዳይፈጠሩ ሊያደርጉ ይችላሉ።

በ2013 የታተመ ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚናገረው ወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች የደም መርጋት ተጋላጭነትን በመጠኑ ሊጨምሩ ይችላሉ። የሰውነት ውስጥ ደም መርጋት የስትሮክ እና ልብ ድካም ተጋላጭነትን ይጨምራል።

ያለማቋረጥ መጠቀም

አብዛኛው ሰው ወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶችን ያለማቋረጥ ለአመታት መውሰድ ይችላል። የመድሃኒቶቹ ክፉ ጎን ጎልቶ ከታየ ግን ዶክተርን በማማከር የመድሃኒት ለውጥ ማድረግ ይቻላል። የደም መርጋት የህክምና ታሪክ ያላቸው ሰዎች የፕሮጄስትሮን ወሊድ መቆጣጠሪያዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ