ጤነኛ

ለቁርጭምጭሚት ህመም የሚረዱ መፍትሄዎች

እረፍት

ለቁርጭምጭሚት በቂ ማገገሚያ ግዜ ይስጡ። ለቀላል የቁርጭምጭሚት ህመም ከ1-2 ቀን ማረፍ በቂ ነው። የህመም ስሜቱ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ከቆየ ዶክተር ያማክሩ።

እረፍትን አለማብዛት

እንቅስቃሴ ለመገጣጠሚያ ጥንካሬ አስፈላጊ ነው። እራሳችንን ከጉዳት የምንከላከልበት አንዱ መንገድ ነው። ቁርጭምጭሚት በቂ እረፍት ካገኘ በኋላ ውጪ ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ መጀመር ያስፈልጋል።

በረዶ

ቁርጭምጭሚት ላይ እብጠት ከተፈጠረ በረዶ ማስደገፍ ይመከራል። ፈሳሽ በውስጡ እንዳይጠራቀም በረዶውን ጠበቅ አድርጎ ማስደገፍ ተገቢ ነው። እብጠቱ እንዳይጨምር እግርን ከፍ አድርጎ ማስተኛት።

ጫማ

kaboompics / Pixabay

የመውደቅ እድልዎን ለመቀነስ ከስር ቆንጥጦ የሚይዝ ጫማ ያድርጉ።

የሰውነት ክብደት

ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ቁርጭምጭሚት ላይ ጫና ይፈጥራል። የአርትራይተስ በሽታ እንዲሁም የጉዳት ተጋላጭነትዎን ይጨምራል። የሰውነት ክብደትን በመጠኑም ቢሆን መቀነስ ቁርጭምጭሚት ላይ ከፍተኛ ለውጥ አለው።

ጡንቻን ማፍታታት

ቁርጭምጭሚት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች በመጥበቅ ለጉዳት ሊያጋልጡን ይችላሉ። እግርን በየቀኑ በማሟሟቅ የጡንቻ ህመምን መቀነስ እንችላለን።

የእንቅልፍ አቋም

በጎን የሚተኙ ከሆነ በቁርጭምጭሚትዎ መሃል ትራስ አስቀምጠው ይተኙ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ