ጤነኛ

ቶንሲል ማስወጣት ያለው ጥቅሞች እና ጉዳቶች

በልጅነት እድሜ ቶንሲል በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ከሚደረግባቸው ምክንያቶች ውስጥ የጆሮ ህመም እና የመተንፈስ ችግር ተጠቃሽ ናቸው። ነገር ግን ቶንሲል ማስወጣት የሚያስከትለው ችግር አለ? የአዲስ ጥናት መሪ የሆነው ተመራማሪ ሾን ቢያርስ የሚከተለውን ይላል፦

“በጥናታችን ማየት እንደቻልነው ቶንሲል ማስወጣት እስከ 30 አመት እድሜ ለትንፋሽ ህመሞች፣ ለአለርጂ እና ኢንፌክሽኖች ይበልጥ ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጋል።” እነዚህ የትንፋሽ ህመሞች አስም እና የሳንባ ምችን ያጠቃልላሉ።

ቀዶ ህክምናውን ከማከናወን በፊት ይህንን የህመሞች ተጋላጭነት ከግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው። ተመራማሪ ቢያርስ እንዲህ ሲል ይመክራል፦

“ጥናታችን የሚጠቁመው ቀዶ-ህክምናውን በተቻለ መጠን በልጅነት እንዳይደረግ ነው።”

ጥናቱ በዴንማርክ ሃገር በልጅነታቸው ቶንሲላቸውን ያስወጡ 60,000 ሰዎች ላይ የተደረገ ሲሆን ተመራማሪዎቹ የተካፋዮቹን ጤነነት ለ30 አመት ሲከታተሉ ቆይተዋል። ቶንሲል ያስወጡ ሰዎች በቶንሲላይተስ በሽታ እና የእንቅልፍ ችግር የመጠቃት እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን መረዳት ቢቻልም እንደ ሳይነስ ላሉ ህመሞች ግን ተጋላጭነት እንደሚጨምር ማየት ተችሏል።

ቶንሲል እና አዴኖይድ መውጣታቸውን ተከትሎ የላይኛው የመተንፈሻ አካሎች በህመም የመጠቃት እድላቸው በሁለት እጥፍ እንደሚጨምር ተመራማሪዎቹ መታዘብ ችለዋል። ኢንፌክሽን እና የአለርጂ ችግሮች የመከሰት እድላቸው ከፍ ብለው ታይተዋል።

ቶንሲሎች ጉሮሮ ጀርባ የሚገኙ ሁለት ክብ እብጠቶች ሲሆኑ አዴኖይድ የሚባሉት አካሎች በጉሮሮ ውስጥ ወደ ላይ ስንሄድ ከአፍንጫ ጀርባ የሚገኙ አካላት ናቸው። ቶንሲል እና አዴኖይዶች የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን የሚደግፉ አካላት ናቸው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ