ጤነኛ

የኩላሊትን ጤንነት እንዴት መጠበቅ እንችላለን

ኩላሊቶች ስራቸውን ሙሉ ቀን ሲያከናውኑ ይውላሉ። ኩላሊትን መንከባከብ ለዘላቂ ጤና በጣም አስፈላጊ ነው። የሚከተሉትን ነገሮች መተግበር ለኩላሊት ጤና ከፍተኛ እንድምታ አለው።

ደም ግፊትን መቆጣጠር

rawpixel / Pixabay

ከፍተኛ ደም ግፊት ኩላሊት ላይ ጫና ይፈጥራል። ሳያውቁ ከፍተኛ ደም ግፊት ሊኖረዎት ይችላል። ዶክተር ጋር በመሄድ የግፊት መጠንን ማወቅ ይመከራል። ለኩላሊት በሽታ ከዋነኛ መንስኤዎች ውስጥ አንዱ ከፍተኛ ደም ግፊት ነው።

ስኳር በሽታ

TesaPhotography / Pixabay

ስኳር በሽታ ካለብዎ ከዶክተር ጋር አብሮ በመስራት የደም ስኳር መጠንዎን ዝቅ ለማድረግ ይሞክሩ። የደም ስኳር መጠን በቁጥጥር ስር ካልዋለ ከግዜ ጋር ኩላሊት እየተጎዳ ይመጣል። ከደም ግፊት ጋር አብሮ የስኳር በሽታ ለኩላሊት በሽታ ዋነኛ መንስኤ ነው።

መድሃኒቶችን መውሰድ

ለኩላሊት ህመም የታዘዘለዎት መድሃኒት ካለ ሳያዛንፉ ተከታትሎ መውሰድ ተገቢ ነው።

ምግብ እና እንቅስቃሴ

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጥቅማቸው ለልብ እና ለሰውነት ክብደት ብቻ አይደለም። የደም ግፊት እና የደም ስኳር መጠንን በመቆጣጠር የኩላሊት ጤናን ለመጠበቅ ይረዳሉ።

ጨው መቀነስ

andreas160578 / Pixabay

የሚወስዱትን የጨው መጠን ይቀንሱ። በቀን ከ2,300 ሚሊግራም በላይ አይመገቡ። የታሸገ ምግብ ሲገዙ ምን ያህል ጨው በውስጡ እንደያዘ ያስተውሉ። ካሰቡት በላይ ሊሆን ይችላል።

ውሃ

በቀን ውስጥ በቂ ፈሳሽ ማግኘት ለኩላሊት አስፈላጊ ነገር ነው። ከአቅም በላይ ውሃ መጠጣት ደግሞ በአንጻሩ ጉዳቱ ያመዝናል። ሽንት በቂ ውሃ ማግኘት አለማግኘትዎን ይጠቁማል። የሽንት ቀለም ነጭ ወይም የደበዘዘ ቢጫ ሲሆን ችግር የለውም። የሽንት ቀለም ጥቁር ቢጫ በሚሆን ግዜ ግን የሚወስዱትን የውሃ መጠን መጨመር ይኖርብዎታል።

አልኮል መጠጣት

ሴቶች በቀን ከአንድ ጠርሙስ አልኮል በላይ እንዳይጠጡ ይመክራል። ወንዶች ደግሞ ከሁለት ጠርሙስ በላይ እንዳይጠጡ የመከራል።

አለማጨስ

geralt / Pixabay

ማጨስ ወደ ኩላሊት የሚሄዱትን የደም ቧንቧዎች ይጎዳል። አጫሽ ከሆኑ የህይወትዎ አንደኛ እቅድ አድርገው ማጨስ ለማቆም ይሞክሩ።

ዘወትር ለምርመራ ወደ ዶክተር መሄድ

ዶክተር በቼክአፕ ግዜ ከሚያደርጋቸው ምርመራዎች አንዱ የኩላሊት ጤናን መመርመር ነው። ኩላሊት የማጣራት ስራውን ምን ያህል ይሰራል የሚለውን ለማወቅ የደም ምርመራ ሊታዘዝ ይችላል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ