ጤነኛ

ስለ ጀርባ ህመም ዘወትር የሚሰጡ 7 የተሳሳቱ ምክሮች

በጀርባ ህመም ዙርያ ብዙ የተሳሳተ መረጃ አለ። አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጀርባን እንደሚጎዳ ብዙ ግዜ እንሰማለን። ጀርባ ህመም ሊስተካከል የሚችለው በቀዶ ጥገና ብቻ እንደሆነ ሌላ የሚነሳ ሃሳብ ነው።

ጀርባ ህመም ብዙ ሰዎች ላይ የሚታይ ችግር ነው። ጀርባ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ የሚከተሉትን እውነታዎች ማስተዋል ተገቢ ነው።

ስህተት 1: አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጀርባን ሊጎዳ ይችላል

እውነታ፡ ስፖርትን በአግባቡ መስራት የጀርባ ጡንቻዎችን በማጠንከር ጀርባን ይበልጥ ያጠናክራል። የጠነከረ ጀርባ ከፍ ያለ ጫናን መቋቋም ይችላል። እንዲሁም የጀርባ አጥንትን አስተካክሎ ይደግፋል።

ስህተት 2: የተንሸራተተ ዲስክ ሊጠገን የሚችለው በቀዶ ጥገና ብቻ ነው

እውነታ፡ በጀርባ አጥንቶች መሃል የሚገኙት ዲስኮች ጀርባ አጥንትን ከከፍተኛ ጫና ይከላከላሉ። የዲስክ ውጪኛ ቅርፊት ሲደክም ዲስክ ሊቀደድ ይችላል። ይህ ሲሆን ዲስክ ውስጥ የሚገኝ ወፍራም ፈሳሽ ወደ ውጪ በመፍሰስ አካባቢው የሚገኙ ነርቮችን ያስቆጣል። በዚህ ግዜ የጀርባ እና የእግር ህመም ይፈጠራል።

ዘጠና በመቶ የሚሆነው የዲስክ መንሸራተት ህመም በእረፍት እና ማስታገሻ መድሃኒቶች አማካኝነት በራሱ ግዜ ያገግማል።

ስህተት 3: የጀርባ ሃኪም ጋር ከሄድኩ ቀዶ ጥገና ይታዘዝልኛል

እውነታ፡ እንደውም የጀርባ ሃኪሞች ታካሚዎች የጀርባ ቀዶ ጥገና እንዳያደርጉ ለማግባባት ይሞክራሉ። ቀዶ-ጥገና ብቸኛ አማራጭ የሆነባቸው የጀርባ ህመም አይነቶች ቢኖሩም አብዛኛው የጀርባ ህመም ያለ ቀዶ-ጥገና የሚስተካከል ነው።

ስህተት 4: የዲስክ ማበጥ የከፍተኛ ጀርባ ህመም ምልክት ነው

እውነታ፡ እድሜ ሲገፋ የጀርባ ዲስክ በራሱ ግዜ ማበጥ ይጀምራል። በዚህ ረገድ ዲስክ ከመኪና ጎማ ጋር ይመሳሰላል። ረጅም ግዜ የተጠቀምነው የመኪና ጎማ ዝቅ ማለት እንደሚጀምረው ሁሉ እድሜም ሲገፋ በዲስክ ምክንያት ቁመታችን እያጠረ ይመጣል።

ስህተት 5: የኤምአርአይ(MRI) ማሽን የጀርባ ህመምን መንስኤ ሁሌ ያሳያል

እውነታ፡ አኑዋል መቀደድ፣ ዲስክ መንሸራተት እንዲሁም የነርቭ መታመቅ በኤምአርአይ ማሽን ሊታወቁ የሚችሉ ችግሮች ናቸው። ኤምአርአይ የጡንቻ መዳከምንም ሆነ ለጀርባ ህመም የሚዳርጉ ሌሎች መንስኤዎችን አያሳይም። የጀርባ ህመም መንስኤን ለማወቅ ሙሉ የሰውነት ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል።

ስህተት 6: በጀርባ መተኛት ለጀርባ ህመም መፍትሄ ይሆናል

እውነታ፡ ለጀርባ ህመም የሚመከረው ቀለል ያለ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው። መራመድ ጀርባ ቀጥ እንዲል ያደርጋል። መንጠራራት እና ሰውነትን ማሟሟቅ ለጀርባ ጤና ይመከራሉ።

ስህተት 7: የነርቭ መቆንጠጥ ሁልግዜ የጀርባ ህመም ይፈጥራል

እውነታ፡ ይህ እውነት ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን የነርቭ መቆንጠጥ ብዙ ግዜ ህመም የሚፈጥረው እግር ላይ ነው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ