ጤነኛ

ሆድ ሲቆጣ መመገብ ያለብዎ 5 ምግቦች

ሆድ ህመም ከተለያዩ የህመም ምልክቶች ጋር አብሮ ሊፈጠር ይችላል። ማቅለሽለሽ፣ የሆድ መነፋት፣ ተቅማጥ ወዘተ። በዚህ ግዜ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ የሚመከር ሲሆን አንዳንድ ምግቦች ለሆድ ጤና የሚሰጡት ጥቅም የጎላ ነው።

ሙዝ

StockSnap / Pixabay

ማራቶን ሯጮች ሙዝን የሚያዘወትሩበት ምክንያት አለ። ሙዝ በቀላሉ የሚፈጭ ምግብ ሲሆን ሆድ በቀላሉ እንዲቆጣ አያደርግም። ሙዝ በተለይ በውስጡ ፔክቲን የሚባል ለሆድ ማብላላት የሚረዳ ንጥረ ነገር ይይዛል።

ፓፓያ

stevepb / Pixabay

ፓፓያ የሆድ መፍጨትን ብቃት የሚያግዝ ምግብ ነው። ከሆድ ድርቀትም ይከላከላል። በውስጡ የያዛቸው ፓፓይን እና ቻይሞፓፒን የሚባሉ ኢንዛይሞች ፕሮቲኖች እንዲዋሃዱ በማድረግ ይታወቃሉ። ሆድ ጤነኛ የአሲዳማ ይዘት እንዲኖረው ያደርጋሉ።

ነጭ ሩዝ

congerdesign / Pixabay

ሆድ በተቆጣበት ግዜ ነጭ ሩዝ፣ ቶስት እና የተቀቀለ ድንች መመገብ ይመከራል። እነዚህ ምግቦች ሆድ ላይ ጫና አይፈጥሩም። ከዛም አልፎ ተቅማጥን በመጠኑም ቢሆን ያስታግሳሉ። ፈሳሽ የመምጠጥ ችሎታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ሰገራ ደረቅ እንዲል ያደርጋሉ።

ዝንጅብል

congerdesign / Pixabay

የተለያዩ ምርምሮች እንደሚጠቁሙት ዝንጅብል የማቅለሽለሽ ስሜትን በማስታገስ እና የሆድ መፍጨት ችሎታን በማገዝ ይታወቃል። የጤና ባለሙያዎች ከሆድ መመረዝ በኋላ ዝንጅብል እንድንበላ ይመክራሉ።

አረንጓዴ ሻይ

rawpixel / Pixabay

ፔፐርሚንት እና ካሞሚል ሻዮች የሆድ ህመምን በማስታገስ ይታወቃሉ። ፔፐርሚንት ሻይ ለሆድ ከሚሰጠው ጥቅም አልፎ የቆሰለ ጉሮሮን ለማከም ይረዳል። ካሞሚል ሻይም ቢሆን የሆድ ህመምን በማስታገስ ይታወቃል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ