ጤነኛ

የትከሻ ህመም መንስኤዎች እና ህክምናቸው

የትከሻ ህመም የቀን ኑሮአችንን ሊያውክ ይችላል። ቁሶችን ማንሳት፣ መኪና መንዳት ወይም ጸጉር ማበጠር ልንቸገር እንችላለን። የማይጠፋ የትከሻ ህመም ካለብዎ ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።

የትከሻ ህመም የተለያዩ መንስኤዎች አሉት። ከነዚህ ውስጥ ብዙ ግዜ የሚፈጠሩት የሮቴተር ከፍ(Rotator cuff) ጉዳት፣ የሮቴተር ከፍ መቀደድ እና ኦስቲⶊርትራይተስ ናቸው።

የሮቴተር ከፍ ጉዳት

ሮቴተር ከፍ የሚባለው የትከሻ ክፍል የአራት ጡንቻዎች እና የጅማታቸው ቅልቅል ነው።

የሮቴተር ከፍ ጉዳት የሚፈጠረው ትከሻን አብዝቶ ከመጠቀም ነው። የሮቴተር ከፍ ጅማቶች ይቆጣሉ ወይም ያብጣሉ። ይህ ሲሆን የትከሻ ፊት እና ጎን ላይ ህመም ስሜት ይፈጠራል። የመዛል ስሜት አብሮ ሊፈጠር ይችላል።

እነዚህ ህመሞች ብዙ ግዜ የሚፈጠሩት እጅን ከፍ አድርጎ በመጠቀም ነው። ቴኒስ መጫወት፣ ዮጋ መስራት እንዲሁም የቤት ቀለም መቀባት ለህመሙ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ናቸው።

እነዚህ ህመሞች ሲፈጠሩ በቂ እረፍት መውሰድ፣ በረዶ ማስደገፍ እንዲሁም እንደ አድቪል አይነት የህመም መድሃኒቶችን መውሰድ ይመከራል። አብዛኛው ሰው ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ያገግማል።

የሮቴተር ከፍ መቀደድ

ምሽት ላይ አላስተኛ የሚል የትከሻ ህመም ከተሰማዎት መንስኤው የሮቴተር ከፍ ጅማቶች ላይ ይተፈጠረ መቀደድ ሊሆን ይችላል።

እጅዎን ከሰውነትዎ በላይ ከፍ ሲያደርጉ የህመም ወይም የድካም ስሜት ከተሰማዎ ይህ ጉዳት አጋጥሞት ይሆናል።

የሮቴተር ከፍ መቀደድ በትከሻ መውደቅ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል። የትከሻ እንቅስቃሴን አብዝቶ መደጋገም ሌላ መንስኤ ነው።

እረፍት፣ በረዶ እና የህመም መድሃኒቶችን መውሰድ ይመከራል።

ኦስቲⶊርትራይተስ(Osteoarthritis)

ይህ ህመም የሚፈጠረው ትከሻን ደግፎ የሚይዘው ልማጽም እየሳሳ ህመም ሲፈጥር ነው።

ይህ በሽታ የትከሻ ጀርባ ላይ ጥልቅ የሆነ ህመም ይፈጥራል። ከግዜ በኋላ እጅን ወደ ጀርባ መላክ እየከበደ ይመጣል።

የዚህ በሽታ ምልክቶች ከግዜ ጋር እየጠነከሩ ይመጣሉ። የህክምና አማራጮች ከሌሎቹ የትከሻ ጉዳቶች ህክምናዎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው። እረፍት፣ በረዶ እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች። ህመሙ ከአቅም በላይ ከበረታ የትከሻ መገጣጠሚያ ቀዶ-ጥገና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ