ጤነኛ

እነዚህን ምግቦች ከማዘጋጀትዎ በፊት ማጠብ የለብዎትም

ዶሮ እና አሳ

RitaE / Pixabay

ዶሮን ከማብሰልዎ በፊት ማጠብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ማጠቡ ባክቴሪያን አያስወግድም። ይልቁኑ ባክቴሪያዎችን ወዳጠቡበት እቃ ያዛምዳል። በዛው እቃ ሌላ ምግብ ማጠብ ባክቴሪያዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል። ባክቴሪያ ከምግብ የሚወገድበት ብቸኛው መንገድ ማብሰል ነው። ማጠብ ካለብዎ ለይተው ከሌላ ምግብ ጋር በማይነካካ እቃ ይጠቡ።

ቀይ ስጋ

tomwieden / Pixabay

ቀይ ስጋም እንደ ዶሮ እና አሳ ሲታጠብ የባክቴሪያ ብክለት ሊፈጥር ይችላል። ከዛም አልፎ ቀይ ስጋ ላይ ያለው ውሃ ስቲም በመፍጠር ጣእሙን ይቀይረዋል።

ፓስታ

JESHOOTScom / Pixabay

ብዙ ሰዎች የተቀቀለን ፓስታ ከማቅረባቸው በፊት ውሃ ያፈሱበታል። እንደዚህ ማድረግ አይመከርም። ፓስታ በውሃ ሲለቀለቅ እላዩ ላይ የሚገኘው ስታርች ይወገዳል። የቲማቲም ድልህ ከፓስታው ጋር በቀላሉ እንዳይወሃድ ያደርጋል። ፓስታን ካጠቡ ከማብሰልዎ በፊት ይጠቡት።

ታጥቦ የታሸገ ምግብ

Couleur / Pixabay

እሽጋቸው ላይ “prewashed” ወይም “triple-washed” ምልክት ያለባቸው ምግቦች ታጥበው የመጡ ምግቦች ናችው። ደግሞ ማጠብ አስፈላጊ አይደለም። ከሌሎች ምግቦች ጋር አብሮ ማጠብ በባክቴሪያ እንዲበከሉ ሊያደርግ ይችላል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ