ጤነኛ

ቦርጭ ማጥፋት ከብዶኛል? ምክንያቱ ምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች ቦርጭ ማጥፋት የሚፈልጉት ለእይታ የሚስብ ተክለቁመና እንዲኖራቸው ቢሆንም የቦርጭ ማጥፋት ጥቅም ከመልክ ይልቅ ለጤና ነው። ከፍተኛ የሆድ ቦርጭ ከልብ በሽታ፣ ስኳር በሽታ፣ ኢንሱሊን ሬዚዝታንስ እና አንዳንድ ካንሰሮች ጋር ግንኙነት አለው። በአመጋገብ እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ቦርጭ ማጥፋት ከተቸገሩ የሆርሞን ችግር ወይም ሌላ የጄኔቲክ ምክንያት ሊኖር ይችላል። በዚህ ጽሁፍ ብዙ ሰዎች የሆድ ቦርጭ ለማጥፋት የሚቸገሩባቸውን ዋነኛ ምክንያቶች እንዳስሳለን።

እድሜ እየገፋ ነው

subhamshome28 / Pixabay

እድሜ በገፋ ቁጥር ሰውነት ክብደት የሚጨምርበትን እና የሚቀንስበትን መንገድ ይቀይራል። ሜታቦሊዝም እየወረደ ይመጣል። ሰውነት ስራውን በስርአቱ ለመስራት የሚያስፈልገው የካሎሪ መጠን ይወርዳል። ሴቶች በተለይ ሲያርጡ ክብደት ሆዳቸው ላይ ክብደት ማጠራቀም ይጀምራሉ።

የሚያስፈልጉ እንቅስቃሴዎችን አለመስራት

AberroCreative / Pixabay

እንደ ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክል አይነት የካርዲዮ እንቅስቃሴዎች ክብደት ለመቀነስ አስፈላጊን ቢሆኑም በነሱ ብቻ ክብደት መቀነስ አስቸጋሪ ነው። የክብደት ስፖርት ከካርዲዮ እንቅስቃሴዎች ጋር ቀላቅሎ መስራት አስፈላጊ ነው። የክብደት እንቅስቃሴዎች ጡንቻ እንዲጨምሩ በማድረግ ሰውነት ይበልጥ ስብ እንዲያቃጥል ያደርጋሉ። በሳምንት ለ250 ደቂቃ መሃከለኛ ጥረት የሚጠይቅ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ይመከራል።

የሚበሉት ምግብ

beernc29 / Pixabay

ነጭ ዳቦ፣ ጣፋጭ ምግቦች፣ ስኳር የበዛባቸው መጠጦች ሰውነታችን ውስጥ የሚከሰተውን ኢንፍላሜሽን ይጨምራሉ ትላለች ክሊቭላንድ ክሊኒክ የምትሰራው ዶክተር ኬት ፓተን። ኢንፍላሜሽን ከሰውነት ክብደት መጨመር ጋር ዝምድና አለው። ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ክብደት ለመቀነስ የሚያረጉትን ጥረት ያስተጓጉላል። ፍራፍሬ እና አትክልቶችን እንዲሁም የአንቲኦክሲዳንት ባህሪያቸው ከፍተኛ የሆኑ ሆል ግሬን ምግቦችን መመገብ ክብደት ለመቅነስ ይመከራል።

የሚበሉት የስብ አይነት

u_rt5bpvly / Pixabay

ስጋ እና የወተት ምርቶች ውስጥ የሚገኘው ሳቹሬትድ ስብ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል። በሌላ በኩል ግን ኦሊቭ ኦይል እና አቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ሞኖሳቹሬትድ ስብ ለጤና ተስማሚ ነው። በመጠኑ መመገብ ለሰውነት የሚሰጠው ጥቅም የጎላ ነው። ሁሉም የስብ አይነቶች ክብደት ለመጨመር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ቢሆንም ጠቃሚዎቹን ስቦች በመጠኑ መመገብ ይመከራል።

በቂ አካል ብቃት እንቅስቃሴ አይሰሩም

ZOE-Animation-Studio / Pixabay

ለረጅም ግዜ የቆየን የሆድ ስብ ለማጥፋት የሚሰሩትን አካል ብቃት እንቅስቃሴ መጨመር ይኖርብዎታል። ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቁ እንቅስቃሴዎች ይበልጥ የሆድ ስብ ያጠፋሉ። ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቁ አካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በፍጥነት ካሎሪ ለማጥፋት ይረዳሉ።

የተሳሳቱ እንቅስቃሴዎችን መስራት

alvoi / Pixabay

እንደ ክራንች አይነት ሆድን በማጠፍ የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎች ቦርጭ አያጠፉም። ይልቅ እንደ ፕላክ አይነት እንቅስቃሴዎች የተሻለ ውጤት አላቸው።

ጭንቀት

TheDigitalArtist / Pixabay

ከፍተኛ ጭንቀት ክብደት ከመቀነስ ሊያግድዎ ይችላል። በጭንቀት ግዜ የሚወስዱት የካሎሪ መጠን ይጨምራል። ከሱም አልፎ የኮርቲዞል ሆርሞን በሰውነትዎ የሚገኘውን የስብ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ከፍተኛ የኮርቲዞል መጠን ከቦርጭ ጋር ይያያዛል።

በቂ እንቅልፍ አለመግኘት

70,000 ሴቶችን ያሳተፈ የ16 አመት ጥናት እንደሚናገረው በቀን ከ5ሰአት በታች እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ከ7ሰአት በላይ ከሚተኙ ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ በ30ፓውንድ ክብደት የመጨመር እድላቸው በ30ፐርሰንት የሰፋ ነው። በቀን ከ7-8 ሰአት እንቅልፍ እንዲያገኙ ይመከራል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ