ጤነኛ

ቦርጭ ለማጥፋት የሚረዱ 4 እንቅስቃሴዎች

የሚከተሉት እንቅስቃሴዎች ቦርጭ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።

ፕላንክ

victorious_fit / Pixabay

ክንድዎን እና የእግር ጣቶችዎን ብቻ መሬት ላይ አስደግፈው ይያዙ። ቁርጭምጭሚት መሬት መንካት የለበትም። ዳሌዎ እና ትከሻዎ ዝቅ ወይም ከፍ እንዳይል ያስተውሉ። በዚህ አቋም ቀጥ ብለው የቻሉትን ያህል ይያዙ።

ገና ጀማሪ ከሆኑ እና መያዝ ከከበደዎ ለ20 ሰከንድ ብቻ ለመያዝ ይሞክሩ። ቀስ በቀስ አንድ ደቂቃ ያህል ለመያዝ ይሞክሩ። እረፍት እየወሰዱ ደጋግመው እንቅስቃሴውን ይስሩ።

የጎን ፕላንክ

HannahWells / Pixabay

መጀመርያ ሰውነትዎን ቀጥ አድርገው በግራ ጎንዎ ይተኙ። እግርዎችዎን ቀጥ አድርገው በትንሹ ያጣምሯቸው። ከዛም በግራ እጅዎ መሬቱን ተጭነው ሰውነትዎን ከፍ ያድርጉ። ቀኝ እጅዎን ወደ ሰማይ ቀጥ አድርገው ይያዙ። በዚህ አቋም መሬት የሚነካው እግሮችዎ እና ግራ እጅዎ ብቻ ነው።

በዚህ አቋም የቻሉትን ያህል ይቆዩ። ሰአትዎን ቀስ በቀስ ለማሻሻል ይሞክሩ።

ረሺያን ትዊስት(Russian twist)

victorious_fit / Pixabay

ሲጀምሩ እግርዎን አጥፈው መሬት ላይ ይቀመጡ። ከዛም በትንሹ ወደ ኋላ ዘንበል ይበሉ። ዘንበል ሲሉ ጀርባዎ ክብ ቅርጽ እንዳይፈጥር። ቀጥ ማለት አለበት። ጀርባዎ ከታጠፈ እንቅስቃሴው አይሰራም። በእጅዎ ክብደት ያለው ነገር ይያዙ። ሲጀምሩ ሁለት ሊትር ፕላስቲክ ውሃ መያዝ ይችላሉ። እቃውን ክንድዎ በታጠፈበት ደረትዎ ፊት አድርገው ይያዙ። በዚህ አቋም እንዳሉ ከሆድ ጀምሮ የላይኛውን ሰውነትዎ ወደ ግራ ያዙሩ። ወደ ግራ እንደዞሩ 3 ሰከንድ ይጠብቁ። ወደ ውስጥ ይተንፍሱ። ከዛም ወደ ቀኝ ይዙሩ። ቀኝ እና ግራ እያፈራረቁ 16 ዙር ያህል ይስሩ።

ተራራ ወጪ(Mountain climbers)

Keifit / Pixabay

ሰውነትዎን በፕላንክ አቋም(የእግር ጣቶች እና ክንዶች ብቻ መሬትን እየነኩ) ያድርጉ። ከዛም ቀኝ ቁርጭምጭሚትን ወደ ደረት ይውሰዱ። የቻሉትን ያህል ወደ ደረት ያቅርቡ። ከዛም በፍጥነት እግርዎን ወደ መጀመርያ አቋሙ ይመልሱ። ከዛም በግራ እግርዎ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ያድርጉ። በፍጥነት እያፈራረቁ መሬት ላይ የመሮጥ እንቅስቃሴ ይስሩ። በዚህ አቋም እያሉ ዳሌ እና ወገብ ወደ መሬት ዝቅ እንዳይል እና ወደ ላይ ከፍ እንዳይል ይጠንቀቁ። ሰውነትዎ ቀጥ ማለት አለበት። በቻሉት ፍጥነት ይስሩ። እረፍት እየወሰዱ እያፈራረቁ ይስሩ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ