ጤነኛ

ለጤና አስፈላጊው አንቲኦክሲዳንት ምንድን ነው? ከየትኛው ምግብ እናገኘዋለን?

አንቲኦክሲዳንቶች(Antioxidant) ምግብ ውስጥ የሚገኙ ንጥረነገሮች ሲሆኑ የሴል ጉዳትን በመከላከል ይታወቃሉ።

ቫይታሚን ሲ፣ ሴሌኒየም እና ቤታ ኬሮቲን የያዙ የተለያዩ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ዋነኛ የአንቲኦክሲዳንት ምንጭ ናቸው። አንቲኦክሲዳንቶች ከበሽታ እንደሚከላከሉ በእርግጠኝነት የተረጋገጠ ባይሆንም የተለየዩ ጥናቶች ፍራፍሬ እና አትክልት አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች በልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች እንዲሁም በካንሰር የመጠቃት እድላቸው ዝቅ ያለ እንደሆነ ይናገራሉ።

ነገር ግን አንቲኦክሲዳንት ክኒኖችን መውሰድ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል ናሽናል ኢንስቲቲውት ኦፍ ሄልዝ ይናገራል። እነዚህ ክኒኖች ከተለያዩ መድሃኒቶች ጋር ይጋጫሉ። እንደ ስትሮክ እና ፕሮስቴት ካንሰር አይነት በሽታዎች ጋር ዝምድና ሊኖራቸው እንደሚችል ይነገራል።

ናሽናል ኢንስቲቲውት ኦፍ ሄልዝ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን አዘውትረን እንድንመገብ ይመክራል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ