ጤነኛ

ጀርሞች በልብስ እና ፎጣ ይተላለፋሉ?

መልሱ እውነት ነው። ጀርሞች በፎጣ እና ልብስ አማካኘነት በ3 መንገዶች ይተላለፋሉ።

  • ፎጣ እና አንሶላ የሚጋሩ ሰዎች ጀርም እርስ በእርስ የማስተላለፋቸው እድል ከፍተኛ ነው
  • አንድ ሰው የሌላን የቆሸሸ ልብስ ሲይዝ ጀርሞች በእጁ አድርገው ልይዙት ይችላሉ
  • የብዙ ሰዎች ልብሶች አብረው ሲታጠቡ ጀርሞች ከአንዱ ወደ ሌላው ሊተላለፉ ይችላሉ

ጀርሞች ፎጣ እና ልብስ ላይ እንዴት ይወጣሉ

congerdesign / Pixabay

ጀርሞች ከሰውነታችን ወደ ልብሳችን ይወጣሉ። ሁላችንም በቆዳችን፣ በአፍንጫችን እና በሆዳችን ባክቴሪያ እንይዛለን። ከነዚህ ባክቴሪያዎች አብዛኞቹ ለጤና ጉዳት የላቸውም። የተወሰኑት ግን በተለይ የቆዳ ቁስል ባለባቸው ሰዎች ላይ ኢንፌክሽን ሊፈጥሩ ይችላሉ።

አብዛኞቹ ጀርሞች ቆዳን ማለፍ ባይችሉም ቆዳ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሊሰፍሩ ይችላሉ። ጀርሞቹን ለማስወገድ እና ከኢንፌክሽን ለመዳን ልብስን ከማጠብ በላይ እጅን መታጠብ አስፈላጊ ነው።

ፓንት ከሁሉም ልብሶች በላይ ጀርሞች የሚገኙበት ልብስ ነው። ፓንት ከሰገራ የሚገኙ ጀርሞች እና ከብልት ኢንፌክሽን የመነጩ ቫይረሶች ይገኙበታል።

ጀርሞች በልብስ አማካኝነት እንዳይተላለፉ ልብስ እና ፎጣን አዘውትሮ በሳሙና ማጠብ ተገቢ ነው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ