ጤነኛ

እነዚህ 10 በሽታዎች በድጋሜ እየተስፋፉ ናቸው

የሳንባ ነቀርሳ ወይም ቲቢ

kalhh / Pixabay

በአለም ዙሪያ በአሁን ግዜ በቲቢ የሚሞተው ሰው ብዛት በ1990 ከሚሞተው ብዛት በግማሽ ያነሰ ነው። ቢሆንም ቲቢ በአለም ዙርያ ብዙ ሰዎችን ከሚገሉ በሽታዎች አንዱ ነው። ቲቪ ለማስቆም የሚደረገው ትግል እየከበደ መቷል። ቲቢን ለማከም የሚውሉት አንቲባዮቲክሶች አዳዲስ የቲቢ አይነቶች ላይ አይሰሩም። ተመራማሪዎች ለበሽታው ዘላቂ መድሃኒት እየፈለጉለት ይገኛሉ።

ቂጥኝ(Syphilis) እና ክላሚዲያ(Chlamydia)

derneuemann / Pixabay

እነዚህን አባላዘር በሽታዎች ለማከም የሚውሉ አንቲባዮቲክሶች ውጤታቸው እንደድሮ አይደለም። ቂጥኝ ብዙ ቦታዎች ለመጥፋት ተቃርቦ ነበር። አሁን ግን እየተመለሰ ይገኛል። ከሁሉም የአባላዘር በሽታዎች በብዛት የሚገኘው ክላሚዲያ ደግሞ ለማከም አስቸጋሪ እየሆነ መቷል። ከሁለቱም በሽታዎች እራሳችንን ለመጠበቅ ኮንዶም መጠቀም ያስፈልጋል።

ስካርሌት ፊቨር(ቀይ ትኩሳት)

By Estreya at English Wikipedia|Permission=CC-BY-2.5; CC-BY-SA-2.5.Modified by Grook Da Oger [GFDL (http://www.gnu.org/copyleft/fdl.html) or CC BY-SA 4.0 (https://creativecommons.org/licenses/by-sa/4.0)], via Wikimedia Commons

ይህም በሽታ ለአንቲባዮቲክሶች ሬዚዝታንስ ባዳበረ ባክቴሪያ ምክንያት ለማከም አስቸጋሪ እየሆነ ያለ በሽታ ነው። በሽታው ከባድ የማይባል ባይሆንም በአብዛኛው እድሜአቸው ከ5-15 አመት የሆናቸውን ልጆች የሚያጠቃ ነው። ቀይ ሽፍታ የሚፈጥር ሲሆን ህክምና ካልተደረገለት የልብ እና የኩላሊት ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

ኩፍኝ

ያልተከተቡ ሰዎች በበሽታው የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ምልክቱ ሰውነትን የሚሸፍን ቀይ ሽፍታ ሲሆን እድሜአቸው ከ5 አመት በታች እና ከ20 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከባድ የጤና ችግር ሊፈጥርባቸው ይችላል። እንደ ሳንባ ምች እና የአንጎል እብጠት ሊያስከትል ይችላል።

ጆሮ ደግፍ

ብዙ ሰዎች ለዚህ በሽታ የተከተቡ ሲሆን ያልተከተቡ ሰዎች የሚኖሩበት ቦታዎች ላይ ወረርሽኝ ሁኖ ይነሳል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት እና የድካም ስሜት ምልክቶቹ ናቸው። ዋናው ምልክቱ ግን አገጭ እና የጉንጭ አጥንት ላይ የሚፈጠር ህመም እና እብጠት ነው። የተለመደ ባይሆንም አንዳንድ ግዜ የአንጎል፣ የጡት፣ የማህጸን እና የዘር ፍሬ እብጠት ሊያስከትል ይችላል።

ደባቅ ሳል(Whooping cough)

ይህ በሽታ ከ10 ሳምንት በላይ በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል። ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ይተላለፋል። ህጻናት በበሽታው ከተጠቁ ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል። ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው።

ሊጂኔርስ በሽታ(Legionnaires’ Disease)

ይህ በሽታ በቅርብ አመታት እየተስፋፋ የመጣ በሽታ ሲሆን የሚከሰተው ሊጅኔላ ባክቴሪያ በውስጣቸው የያዙ ጥቃቅን የውሃ እንክብሎችን በመተንፈስ ነው። ሲጀምር ምልክቶቹ ከብርድ ምልክቶች ጋር ይመሳሰላሉ። እየቆየ ግን የደረት ህመም እና መተንፈስ መቸገር ያስከትላል። አንቲባዮቲክስ ሊያድኑት ይችላሉ። በግዜ ካልተያዘ ግን ከባድ ህመም ላይ ሊጥለን ይችላል።

ስጋ ደዌ

ይህ በሽታ የሚፈጠረው ነርቭን በሚያጠቁ ባክቴሪያዎች አማካኝነት ነው። በየአመቱ በአለም ዙሪያ 250,000 የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ። እጅ እና እግርን ከማንቀሳቀስ ሊያግደን ይችላል። በቀላሉ የማይተላለፍ ሲሆን ለማከም የሚቀል በሽታ ነው።

ሪህ

cnick / Pixabay

ሪህ በቅርብ ግዜ እየተንሰራፋ የመጣ በሽታ ነው። ዶክተሮች የሚጠረጥሩት ምክንያት የማህበረሰቡ ክብደት መጨመር ነው። ከፍተኛ የሰውነት ክብደት በሪህ የመጠቃት እድላችንን በሁለት እጥፍ ይጨምራል። ሪህ ብዙ ግዜ የሚጀምረው የእግር አውራጣት ላይ በሚፈጠር ከባድ ህመም ነው። ነገር ግን ቁርጭምጭሚት እና ክንድ ላይ ሊፈጠር ይችላል።

ሪኬትስ(የአጥንት መለስለስ)

ይህ በሽታ በቫይታሚን ዲ እጥረት ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን የልጆች አጥነት እንዲለሰልስ ምክንያት ይሆናል። በቅርብ አመታት እየጨመረ የመጣ በሽታ ነው። መንስኤዎቹ የጡት ማጥባት ዘይቤ እና የቆዳ ካንሰር ፍራቻ ናቸው። የጡት ወተት ውስጡ ምንም ቫይታሚን ዲ የለውም። ከዛም አልፎ የቆዳ ካንሰር ልጃቸውን እንዳይዛቸው ብለው ልጃቸውን ጸሃይ የማያስነኩ እናቶች ልጅ ቫይታሚን ዲ እንዳያገኝ ያደርጋሉ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ