ጤነኛ

እነዚህን 7 አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች ባገኙት እድል ይመገቡ

የሚከተሉት ምግቦች እያንዳንዳቸው የተለያዩ ለሰውነት የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ። እነዚህን ምግቦች ቀላቅሎ መመገብ ሰውነት በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን ንጥረነገሮች ለማግኘት ያስችለዋል።

ስፒናች

ThiloBecker / Pixabay

ስፒናች የቫይታሚን ኬ፣ ቫይታሚን ኤ፣ አይረን እና ካልሲየም ምንጭ ነው። ከሰላጣ ወይም ፓስታ ጋር አብሮ በመስራት መመገብ ይችላሉ። ሲገዙ ቀለሙ ቢጫ ያለሆነውን መርጠው ይግዙ። ስፒናች መታጠብ ያለበት ለምግብ ተዘጋጅቶ ከመቅረቡ በፊት ነው። አጥቦ ማስቀመጥ አይመከርም።

ጥቁር ጎመን

WikimediaImages / Pixabay

ጥቁር ጎመን በውስጡ ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ኬ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኢ፣ ቫይታሚን ቢ2, ፖታሲየም፣ ካልሲየም እና ፋይበር ይይዛል።

ጥቁር ጎመን ፍሪጅ ውስጥ ከ5 ቀን በላይ ባይቀመጥ ይመከራል። ለረጅም ግዜ ሲቀመጥ መጎምዘዝ ይጀምራል።

ቀይ ቃሪያ

JESHOOTScom / Pixabay

ቀይ ቃሪያ የቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ቢ6፣ ቫይታሚን ሲ እና የፋይበር ምንጭ ነው። ከሰላጣ ጋር አብሮ ማዘጋጀት ይመረጣል።

አበባ ጎመን

Couleur / Pixabay

አበባ ጎመን በውስጡ ቫይታሚን ቢ5፣ ኮሊን፣ ፋይበር እና ማንጋኒዝ ይይዛል። ነጭ ወይም ክሬም ቀለም ያለው አበባ ጎመን ይመከራል። በሳላድ መልክ ሊዘጋጅ ይችላል።

ቲማቲም

stevepb / Pixabay

ቲማቲም የቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ኬ፣ ባዮቲን፣ ኮፐር፣ ፖታሲየም እና ማንጋኒዝ ምንጭ ነው። ከሰላጣ ጋር አብሮ ሊዘጋጅ ይችላል።

ቀይ እንጆሪ(Strawberry)

Engin_Akyurt / Pixabay

ስትሮቤሪ በውስጡ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ቢ6፣ ማንጋኒዝ፣ ፋይበር፣ ፎሌት፣ ኮፐር እና ፎስፈረስ ይይዛል። ስትሮቤሪ በጁስ መልክ ወይም በጥሬው ሊመገቡ ይችላሉ። ከፓንኬክም ጋር አብሮ ሊቀርብ ይችላል። ፍሪጅ ውስጥ የተቀመጠን ቀይ እንጆሪ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ መመገብ ተገቢ ነው።

ባህር ሎሚ(Grapefruit)

Couleur / Pixabay

የባህር ሎሚ በውስጡ ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ቢ5 እና ኮፐር ይይዛል። የባህር ሎሚን ከአትክልት ሳላድ ወይም ከፍራፍሬ ሳላድ ጋር ቀላቅሎ ማቅረብ ይቻላል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ