ጤነኛ

የወር አበባ እንዳለቀ ግንኙነት ማድረግ እርግዝና ያስከትላል?

የወር አበባ እንደጨረስሽ ግንኙነት ብታደርጊ የመጸነስ እድልሽ ዝቅተኛ ነው። ነገር ግን ጽንስ የመፈጠር እድሉ ዝቅተኛ ሆነ እንጂ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለት አይቻልም። ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት በማንኛውም ግዜ ለእርግዝና ያጋልጣል።

ወር አበባ አይታ የማታቅ ሴት እንኳ ልታረግዝ ትችላለች። ሙሉ በሙሉ ከእርግዝና ነጻ የሆነ ግዜ የለም።

የወር አበባ ኡደት

የወር አበባ ከሚታይሽ የመጀመርያው ቀን ጀምር እስከ የሚቀጥለው ዙር የሚታይሽ የመጀመርያው ቀን ያለው ግዜ አንድ የወር አበባ ኡደት ነው። ከየትኛውም ግዜ በላይ ለእርግዝና ዝግጁ የሆንሽው መጀመርያ ወር አበባ ካየሽበት ከ12-14 ቀን በኋላ ነው። ወር አበባ ከጀመረሽበት ቀን ጀምሮ ለሚከተሉት የተወሰኑ ቀናት የማርገዝ እድልሽ አነስተኛ ነው። የወንድ የዘር ሴል በሴት ማህጸን ውስጥ እስከ 7 ቀን በህይወት ሊቆይ ይችላል። በዚህ ምክንያት የወር አበባ የጨረሽበት ሰሞን ግንኙነት ካደረግሽ ልታረግዢ ትችያለሽ። በተለይ ደግሞ የወር አበባ ኡደት ግዜሽ አጭር ከሆነ የማርገዝ እድልሽ ሰፊ ነው።

ያለተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ምንግዜም የወሊድ መቆጣጠሪያ ወይም ኮንዶም መጠቀም ተገቢ ነው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ