ጤነኛ

የአንጎል ስብራት(Concussion) ምልክቶች

በየአመቱ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ልጆች የአንጎል ስብራት ያጋጥማቸዋል። አንጎል ስብራት በመውደቅ፣ ስፖርት ላይ በሚፈጠር ግጭት፣ ጭንቅላትን በመመታት እንዲሁም ከተለያዩ ነገሮች ጋር በመጋጨት ይፈጠራል።

ብዙ ሰዎች የማያውቁት ነገር አንጎል ስብራት እንዲፈጠር ግጭቱ ከፍተኛ መሆን እንደሌለበት ነው። አንጎል ስብራት ግጭት ሳይፈጠርም ሊከሰት ይችላል። ጭንቃላት በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀስ ሊከሰት ይችላል። በዚህ ምክንያት እንደ ሄልሜት አይነት የጭንቅላት ሽፋኖች ከአንጎል ስብራት አያድኑም። ሄልሜት ከራስ ቅል ስብራት ቢጠብቀንም የአንጎል ስብራት ተጋላጭነቱ እንዳለ ነው።

ምልክቶች

geralt / Pixabay

የአንጎል ስብራትን(ኮንካሽን) መፈጠሩን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። የአንጎል ስብራት የተለየ ህክምና ባይኖረውም በቂ የሰውነት እና የአእምሮ እረፍት ማድረግ ምልክቶቹ በግዜ እንዲጠፉ ያደርጋል። ተጨማሪ ስብራት እንዳይፈጠር ተገቢውን ጥንቃቄ ለመውሰድ በጣም አስፈላጊ ነው። ስብራቱ ከተፈጠረ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ከስብራቱ እስኪያገግም ድጋሚ ጉዳት እንዳይፈጠር መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተደጋጋሚ ስብራቶች ለዘላቂ አእምሮ ጉዳት ያጋልጣሉ።

የሚከተሉት ምልክቶች ስብራት ከተፈጠረ በኋላ ሊታዩ ይችላሉ።

 • ራስን መሳት ወይም የእንቅልፍ መጠን መጨመር። ከእንቅልፍ መቀስቀስ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
 • ከፍተኛ የጭንቅላት ህመም
 • ማዞር። መቆም እና መራመድ መቸገር
 • ግራ መጋባት፣ ነገሮችን ማስታወስ መቸገር
 • ከፍተኛ የማቅለሽለሽ ስሜት። አንዳንዴ ማስመለስ
 • እንፍርፍሪት

ግልጽ ያልሆኑ ምልክቶች

አንዳንዴ የአንጎል ስብራት ምልክቶች ለማወቅ አሽቸጋሪ ይሆናሉ። የሚከተሉት ምልክቶች ከስብራት በኋላ ለተወሰኑ ሳምንታት ወይም ወራት ሊዘልቁ ይችላሉ።

 • በተደጋጋሚ የሚፈጠር ራስ ምታት
 • በተደጋጋሚ የሚፈጠር የማቅለሽለሽ ስሜት
 • ትኩረት መስጠት መቸገር
 • ነገሮችን ማስታወስ ወይም አዲስ መረጃዎችን መቀበል መቸገር
 • የድካም ስሜት
 • ብስጩ መሆን
 • የእንቅልፍ ችግር – አሳንሶ ወይም አብዝቶ መተኛት
 • ማዞር
 • ብዥታ

እነዚህ ምልክቶች የሌላ በሽታ ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህን ምልክቶች በራስዎ ወይም በሰው ላይ ካዩ ግዜ ሳይሰጡ ዶክተር ያማክሩ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ