ጤነኛ

አንቲባዮቲክ እየወሰድኩ አልኮል መጠጣት እችላለሁ?

አልኮል መጠጥ ከተለያዩ መድሃኒቶች ጋር አብሮ ስለማይሄድ ብዙ ግዜ ከመድሃኒት ጋር አብሮ እንዲወሰድ አይመከርም። ነገር ግን አንቲባዮቲክ እየወሰዱ በመጠኑ አልኮል መጠጣት ችግር አያስከትልም።

ከአልኮል ጋር መወሰድ የሌለባቸው መድሃኒቶች

qimono / Pixabay

እነዚህን መድሃኒቶች ሲወስዱ አልኮል መንካት የለብዎትም።

  • ሜትሮኒዳዞል(metronidazole) – ይህ አንቲባዮቲክ የጥርስ እና የብልት ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም አንዳንድ የእግር ቁስሎችን ለማከም ይውላል።
  • ቲኒዳዞል(tinidazole) – ይህ አንቲባዮቲክ ሜትሮኒዳዞል የሚያክማቸዋን ህመሞች ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል። ኤች ፓይሎሪ የሚባለውን ባክቴሪያ ለማከምም ጥቅም ላይ ይውላል።

አልኮል ከነዚህ መድሃኒቶች ጋር ሲቀላቀል የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያስከትል ይችላል፦

  • የህመም ስሜት
  • የሆድ ህመም
  • የልብ ምት ፍጥነት ለውጥ
  • ራስ ምታት
  • የማዞር ስሜት
  • የድካም ስሜት

ሜትሮኒዳዞልን ከጨረሱ በኋላ አልኮል ከመጠጣትዎ በፊት 48 ሰአት ይጠብቁ። ለቲኒዳዞል ደግሞ 72 ሰአት።

ሌሎች ከአልኮል ጋር ሊቀላቀሉ የሚችሉ መድሃኒቶች

Quadronet_Webdesign / Pixabay

የሚከተሉት መድሃኒቶች ከአንዳንድ የአልኮል መጠጦች ጋር ሊቀላቀሉ ይችላሉ፦

  • ሊንዞሊድ(linezolid) – ሊንዞሊድ እንደ ወይን እና ቢራ አይነት የፈሉ መጠጦች ጋር አብሮ መወሰድ የለበትም
  • ዶክሲሳይክሊን(doxycycline) – ይህ መድሃኒት ከአልኮል ጋር የመቀላቀል ታሪክ አለው። ከአልኮል ጋር ሲወሰድ ውጤታማነቱ ይወርዳል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ