ጤነኛ

ስለ ትዳር በተለምዶ የሚሰነዘሩ 4 የተሳሳቱ አመለካከቶች

ለጥሩ ትዳር አስፈላጊ ናቸው ተብለው የሚነሱ ሃሳቦች እና ምክሮች በርካታ ቢሆኑም በመረጃ የተደገፉት ጥቂቶቹ ናቸው። ብዙ ለትዳር ወሳኝ ተብለው የሚነሱ ሃሳቦች ስህተት ናቸው። ጎትማን ኢንስቲቲውት በሺዎች የሚቆጠሩ ባለትዳሮች ላይ በሰራው ጥናት ስለትዳር ከሚነሱ የተሳሳቱ አመለካከቶች የሚከተሉትን በብዛት ቀዳሚ አድርጓቸዋል።

ስህተት 1 – ባለትዳሮች ተመሳሳይ ነገሮች ቢያዘወትሩ ይመረጣል

MabelAmber / Pixabay

በሰርቬ በተደረጉ ጥናቶች ብዙ ተጠያቂዎች ተመሳሳይ ነገሮች ማዘውተርን እንደ አስፈላጊ የፍቅረኛ መለኪያ አድርገው ያስቀምጣሉ። ነገር ግን ዋናው ነገር አንድ አይነት ነገሮችን ማዘውተር ሳይሆን አንድላይ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ነገር በአጋርነት የሚያደርጉበት መንገድ ነው።

ሁለታችሁም አካል ብቃት እንቅስቃሴ ታዘወትሩ ይሆናል። ነገር ግን አብራቹህ እንቅስቃሴ ከመስራታችሁ በላይ አንድ ላይ የምትሰሩበት መንገድ ወሳኝ ነው። ነቀፋ እና ትችት በሞላበት ሁኔታ ነገሮችን አብራችሁ የምትፈጽሙ ከሆነ የግንኙነታችሁ ዘላቂነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ትችት ባለትዳሮች ከሚለያዩባቸው ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ነው።

ስህተት 2 – ተናዳቹህ ወደ አልጋ አትሂዱ

kabaldesch0 / Pixabay

ችግሮችን ወዲያው ፍቱ ይላል ምክሩ። ተቃርኖን አድበስብሶ ማሳለፍ የሚመከር ባይሆንም አንዳንድ ግዜ ትክክለኛው ውሳኔ የሚፈጠሩ ግጭቶችን ትቶ ማለፍ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ትዳር ውስጥ ለግጭት መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች ውስጥጥ ሁለት ሶስተኞቹ መቼም መፍትሄ አያገኙም። እቃን በማጠብ እና ቤትን በማጽዳት ዙሪያ የሚነሱ ትናንሽ ተቃርኖዎች ብዙ ግዜ መፍትሄ የላቸውም።

በግጭት መሃል የጋለ ስሜት ውስጥ ከገቡ በኋላ ከዛ ስሜት ለመውጣት ግዜ ያስፈልጋል። በዚህ ግዜ እስኪረጋጉ በመቆየት ከተረጋጉ በኋላ ችግሩን መፍታት ይመከራል።

ስህተት 3 – የውጪ እርዳታ ወይም ሽምግልና የሚያስፈልገው ትዳር ከተሰበረ በኋላ ነው

geralt / Pixabay

ብዙ ባለትዳሮች ለትዳራቸው ሸምጋይ የሚፈልጉት ከ6 አመት በኋላ ነው። ነገር ግን አብዛኞቹ ትዳሮች የሚፈርሱት በመጀመርያዎቹ 7 አመታት ውስጥ ነው። አማካሪ እና ሸምጋይ በግዜ ማማከር ትዳርን ከመፍረስ ሊያድን ይችላል።

ስህተት 4 – ለትዳር መፍረስ ዋናው ምክንያት መማገጥ ነው

mohamed_hassan / Pixabay

መማገጥ ለትዳሩ መፍረስ አስተዋጽኦ ቢያደርግም ብዙ ግዜ የትዳሩ መፍረስ ምክንያት አንዱ ሰው ከመማገጡ በፊት የተፈጠረ ችግር ነው። በፍቺ ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚናገረው 80 በመቶ ባለትዳሮች ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት አድርገው ያስቀመጡት በትዳሩ ውስጥ የተፈጠረ የመራራቅ እና የቅርበት ማጣት ስሜት ነው። መማገጥ ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት ነው ያሉት ከ20-27 በመቶ የሚሆኑት ናቸው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ