ጤነኛ

መተኛት ያለብዎ በጀርባ ነው በጎን ወይስ በሆድ

የፋብሪካ ወይም የቀን ሰራተኛ ለረጅም ሰአት ሳይንቀሳቀስ በአንድ አቋም ሲሰራ እራሱን ለጉዳት እንደሚያጋልጠው ሁሉ በአንድ በኩል ብቻ የሚተኛ ሰው እራሱን ለጉዳት ያጋልጣል። በጎን ብቻ መተኛት ለትከሻ ጉዳት ይዳርገናል። በጀርባ ብቻ መተኛት ደግሞ ለጀርባ ጉዳት።

ለጀርባ አጥንት ተስማሚ የሆነው በጀርባ እና በጎን እያፈራረቁ መተኛት ሲሆን በሆድ መተኛት አይመከርም።

በጀርባ መተኛት

ከሁሉም አቋሞች በጀርባ መተኛት ለጀርባ አጥንት ተስማሚ ነው። በጀርባ ህመም ምክንያት በጀርባቸው መተኛት የሚቸገሩ ሰዎች ቁርጭምጭሚታቸው ስር ትራስ እንዲያደርጉ ይመከራል።

በጎን መተኛት

በጎን ሲተኙ አንገትዎን ቀጥ አድርገው እንዲተኙ ይመከራል። አገጭን ወደ አንገት አጥፎ መተኛት የአንገት ህመም ይፈጥራል።

በሆድ መተኛት

በሆድ ሲተኙ ጭንቅላትዎ ወደ አንድ በኩል ስለሚዞር ለአንገት ህመም ይዳርጋል። በቆሙበት ጭንቅላትዎን ለረጅም ሰአት ወደ አንድ በኩል ማዞር ህመም እንደሚፈጥረው ሁሉ በእንቅልፍ ግዜ ጭንቅላትን አዙሮ መተኛት ተመሳሳይ የአንገት ጫና ይፈጥራል። በሆድ መተኛት ደም ወደ እጅ እንዳይደርስ የሚያደርግ ተጽእኖ ይፈጥራል።

በሆድ በተኙበት አንድ እግርን አጥፎ ሌላኛው እግር ላይ መደረብ ዳሌ እና ታችኛው ጀርባ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ለቁስለት ሊዳርግ ይችላል። በሆድ መተኛት ከለመዱ ልምዱን ለመስበር በጎን መተኛት ይጀምሩ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ