ጤነኛ

ሁሉም ኦቾሎኒ ቅቤ ለጤና ተስማሚ አይደለም። ትክክለኛውን የሚመርጡበት መንገድ።

የኦቾሎኒ ቅቤ በዳቦም ቀብተን በላነው ከሙዝ ጋር ፈጭተን በጁስ መልክ ወሰድነው ብዙ ጥቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ምግብ ነው። አቾሎኒ ቅቤ የፕሮቲን ምንጭ ብቻ አይደለም። በውስጡ በርካታ ንጠረነገሮችን የያዘ ምግብ ነው። ጠቃሚ ስቦች፣ ቫይታሚን ኢ፣ ማግኒዚየም፣ ፖታሲየም እና ቫይታሚን ቢ6ን የያዘ ነው። ነገር ግን በምንገዛበት ወቅት ለጤና ተስማሚ የሆነውን መርጠን መሆን አለበት።

ምርጫ

OpenClipart-Vectors / Pixabay
  • በእሽጉ ላይ ሃይድሮጅኔትድ ዘይት(Hydrogenated oil) አለመኖሩን ያረጋግጡ። ይህ ንጥረ ነገር ለጤና ጎጂ የሆነውን ትራንስ ፋት በውስጡ ይይዛል።
  • አንዳንድ የኦቾሎኒ ቅቤ እሽጎች በውስጣቸው ስኳር ይይዛሉ። ሲገዙ ከ3ግራም ስኳር በታች ያለውን ኦቾሎኒ ቅቤ ይግዙ።
  • ኦቾሎኒ ብቻ ያለውን ቅቤ ይግዙ። ስኳር እና ስብ ያልተቀላቀለበት ቅቤ ቢገዙ ይመረጣል።
  • ሲመገቡ ከኦቾሎኒ ቅቤ እሽጉ ቀጥታ አይመገቡ። ኦቾሎኒ ቅቤ የካሎሪ መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ በማንኪያ መብላት ከሚያስፈልግዎ ካሎሪ በላይ እንዲወስዱ ምክንያት ይሆናል

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ