ጤነኛ

እነዚህን 9 ምግቦች መመገብ ያቁሙ

አዘውትረን ከምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ ጉዳታቸው የሚያመዝን በርካታ ምግቦች አሉ። እነዚህ ምግቦች በስኳር እና ስብ የተሞሉ ሲሆን የካሎሪ መጠናቸውም ዜሮ ነው።

ለስላሳ መጠጦች

igorovsyannykov / Pixabay

ይተለያዩ ጥናቶች ለስላሳ መጠጦችን መጠጣት እንድንቀንስ ይመክራሉ። የአሜሪካ ዳየቴሪ ጋይድላይን እንደሚናገረው እነዚህ መጠጦች ለክብደት መጨመር ተጠቃሽ ምክንያት ናቸው።

የስብ መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ የኦቾሎኒ ቅቤ

Meditations / Pixabay

የአመጋገብ ባለሙያ የሆነችው ኤሚ ጎሪን የሚከተለውን ትላለች፦

“ኦቾሎኒ ቅቤ የጥጋብ ስሜት የሚፈጥር እና ለልብ የሚስማማ ስብ በውስጡ ይይዛል። ነገር ግን ይህ ስብ በሚወጣበት ወይም በሚቀነስበት ግዜ ተጨማሪ ስኳር እና ሌሎች ንጥረነገሮች አብረው ይጨመራሉ። የኦቾሎኒ ቅቤ በሚገዙበት ግዜ የተጻፈውን በማንበብ የተጠበሰ ኦቾሎኒ ብቻ ያለውን መርጠው ይግዙ።”

ማርጋሪን

doornekamph / Pixabay

ጎሪን ስለማርጋሪን የሚከተለውን አስተያየት ትሰጣለች፦

“ማርጋሪን የገበታ ቅቤ አማራጭ ሁኖ ይቀርባል። ነገር ግን ብዙ የማርጋሪን አይነቶች በውስጣቸው ሃይድሮጅኔትድ ዘይት(Hydrogenated oil) በውስጣቸው ይይዛሉ። ይህ ዘይት በውስጡ ጎጂ የሆኑ ትራንስ ፋቶችን የያዘ ነው። የኮሌስትሮል መጠንን ይጨምራል፣ ለልብ በሽታ ተጋላጭ ያደርገናል።”

በጣሳ ታሽገው የሚሸጡ ፍራፍሬዎች

serenasampson / Pixabay

የተመጣጠነ አመጋገብ እንዲኖረን ፍራፍሬ መመገብ አስፈላጊ ቢሆንም ፍራፍሬው የሚዘጋጅበት መንገድ ወሳኝ ነው። ጎሪን የሚከተለውን ትላለች፦

“በጣሳ የሚሸጥ ፍራፍሬ እንደሌላው ጠቃሚ ነው ብለን ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን እሽጉ ላይ “light syrup” ወይም “heavy syrup” የሚል ጽሁፍ ካለው ስኳር ተጨምሮበታል ማለት ነው። ፍራፍሬው የታሸገበት ፈሳሽ ውሃ ወይም ጁስ የሆነውን ጣሳ መርጠን ብንገዛ ይመረጣል።”

የጥጥ ከረሜላ

elenagordinskyua / Pixabay

እንደ ዩኤስዲኤ ፉድ ዳታቤዝ የጥጥ ከረሜላ መቶ በመቶ ስኳር ነው። 1አውንስ የሚሆን የጥጥ ከረሜላ በውስጡ 110ካሎሪ እና 28ግራም ስኳር አለው። ይህ ምግብ ቀላል ምግብ ቢመስልም አይደለም። ጥርስም ላይ ጉዳት ይፈጥራል።

ኬክ ላይ የሚደረግ የፍሮስቲንግ ክሬም

Free-Photos / Pixabay

ሁለት የሻይ ማንኪያ የሚሞላ ኬክ ላይ የሚደረግ የቸኮሌት ፍሮስቲንግ በውስጡ 140 ካሎሪ፣ 18 ወይም 19 ግራም ስኳር እና 2 ግራም የሚሆን ሳቹሬትድ ስብ ይይዛል። እንደ ሃይድሮጅኔትድ ስብ አይነት ጎጂ ንጥረነገሮችም በውስጡ ይገኛሉ።

የቡና መጠጦች

adoproducciones / Pixabay

የአመጋገብ ባለሙያ ናታሊ ሪዞ እንደምትለው እንደ ፍራፓቺኖ እና ካራሜል ማኪያቶ አይነት የቡና መጠጦች ባዶ ካሎሪ አላቸው።

“እነዚህ መጠጦች እንደቡና መስለው ቢቀርቡም መታየት ያለባቸው እንደ ዲዘርት ምግብ ነው። አልፎ አልፎ መውሰድ ችግር የለውም። ነገር ግን እንደ ቡና ተተኪ አድርገን አዘውትረን የምንጠቀማቸው ከሆነ ጉዳታቸው ያመዝናል። በስኳር የጣፈጡ መጠጦች ከብዙ ምግቦች የበለጠ ስኳር፣ ስብ እና ካሎሪ ሊይዙ ይችላሉ።”

ነጭ ዳቦ

beernc29 / Pixabay

ነጭ ዳቦ ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የሉትም። እንደ ዩኤስዲኤ የምግብ ዳታቤዝ ከሆነ አንድ በቀጭኑ የተቆረጠ ነጭ ዳቦ 150ካሎሪ የሚይዝ ሲሆን የፋይበር መጠኑ ዝቅተኛ ነው።

ነጭ ቸኮሌት

caja / Pixabay

ቸኮሌት የሚሰጣቸው ጥቅሞች ሁሉ ነጭ ቸኮሌት ውስጥ አይገኙም። አንድ አውንስ ነጭ ቸኮሌት በውስጡ 150 ካሎሪ፣ 5ግራም ሳቹሬትድ ስብ እና 16.5ግራም ስኳር የያዘ ነው። ነጭ ቸኮሌት ለጤና ጠቃሚ የሆነው እና ጥቁር ቸኮሌት ውስጥ የሚገኘውን ኮኮዋ በውስጡ አይዝም።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ