ጤነኛ

6 የቫይታሚን እጥረት ምልክቶች

ምግብ ሳንመርጥ የምንበላ ቢሆን እንኳ ተገቢ ምግቦች ካላገኘን የቫይታሚን እጥረት ሊያጋጥመን ይችላል። የሚከተሉት ምልክቶች የቫይታሚን እጥረት እንዳጋጠመዎት ይጠቁማሉ።

የእጅ ጥፍር መፈረካከስ

Hans / Pixabay

የአይረን እጥረት ሲያጋጥመን የሰውነት አካላት ደካማ ይሆናሉ። ቀለማቸውም ይጠፋል። የሚፈረካከስ የእጅ እና የእግር ጥፍር ሌላ አንዱ ምልክት ነው። የወር አበባ መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ሴቶች ለዚህ ችግር ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

ሴቶች በቀን 18ሚሊግራም አይረን የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ወንዶች እና ያረጡ ሴቶች በቀን 8ሚሊግራም አይረን እንዲያገኙ ይመከራል። ሰውነት ከአትክልት ይልቅ ከእንስሳ የወጣ አይረንን ይበልጥ ጥቅም ላይ ያውለዋል። ስጋ፣ እንቁላል እና አሳ ጥሩ የአይረን ምንጮች ናቸው።

ከፍተኛ የደም ግፊት

rawpixel / Pixabay

የቫይታሚን ዲ እጥረት ለከፍተኛ የደም ግፊት ሊያጋልጥዎት ይችላል። አዋቂዎች በቀን 600 ኢንተርናሽናል ዩኒትስ ያህል ያስፈልጋቸዋል።

‹h2>ዝቅተኛ የደም ግፊት

rawpixel / Pixabay

ዝቅተኛ የደም ግፊት በቫይታሚን ቢ12 እጥረት ምክንያት ሊፈጠር ይችላል። የዚህ ቫይታሚን እጥረት ኒውሮሎጂካል ሲስተም ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል። ያልተስተካከለ ቁመና፣ የጡንቻ ድክመት እና ሽንትን መቆጣጠር አለመቻል ሁሉም የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

አዋቂዎች በቀን 2.4ማይክሮግራም ቫይታሚን ቢ12 ያስፈልጋቸዋል። ስጋ፣ ወተት፣ እንቁላል ጥሩ የቫይታሚን ቢ12 ምንጮች ናቸው።

የእግር ስትራፖ

ሰውነት ጡንቻ እና ፕሮቲን ለማዳበር ኤሌክትሮላይት ፖታሲየም ያስፈልገዋል። በሰውነታችን ውስጥ ያለው የፖታሲየም መጠን ሲቀንስ ባት ዙሪያ የጡንቻ ስትራፖ ያጠቃናል። ብዙ ግዜ የፖታሲየም እጥረት የሚፈጠረው ከፍተኛ ላብ ሲያልበን፣ ሲያስቀምጠን ወይም ሲያስመልሰን ነው።

በቀን 4700 ሚሊግራም ፖታሲየም ማግኘት አለበት። ስኳር ድንች፣ ሙዝ እና አቮካዶ ጥሩ የፖታሲየም ምንጮች ናቸው።

የድካም ስሜት

Free-Photos / Pixabay

የድካም እና የመነጫነጭ ስሜቶች የቫይታሚን ሲ እጥረት ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ሴቶች በቀን 75 ሚሊግራም ቫይታሚን ሲ ሲያስፈልጋቸው፣ ወንዶች 90 ሚሊግራም ያስፈልጋቸዋል። የሚያጨሱ ሰዎች ለቫይታሚን ሲ እጥረት ይበልጥ ተጋላጭ እንደመሆናቸው ተጨማሪ 35 ሚሊግራም ያስፈልጋቸዋል። ብርቱካን፣ አናናስ፣ ቲማቲም እና ቆስጥ ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጮች ናቸው።

የአጥንት ስብራት

Taokinesis / Pixabay

የካልሲየም እጥረት ኦስቲዮፔኒያ ለሚባል በሽታ ያጋልጥዎታል። ይህ ህመም የአጥንትዎን እፍጋት በመቀነስ ለአጥንት ስብራት ያጋልጥዎታል። ክ30 አመት እድሜ በኋላ የአጥንት የካልሲየም መጠን እየቀነሰ ይመጣል።

ወንዶች እና ወጣት ሴቶች በቀን 1000 ሚሊግራም ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። ያረጡ ሴቶች 1200 ሚሊግራም ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። ወተት፣ እርጎ እና ቺዝ የመሳሰሉ የወተት ምርቶች የካልሲየም መጠናቸው ከፍተኛ ነው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ