ጤነኛ

ብቸኝነት የሚያስከትላቸው 10 የጤና ችግሮች

የብቸኝነት ዋነኛ መገለጫ ከሰው ጋር ግዜ አብሮ አለማሳለፍ አይደለም። ብቸኝነት በዋነኝነት የሚገለጸው ከሰዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት በማጣት ነው። በህይወታቸው ጤንነት እና ደስተኝነት የሚሰማቸው ሰዎች ከሰዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው። ብቸኝነት የሚሰማቸው ሰዎች በአንጻሩ የተለያዩ የጤና ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል።

1) የሰውነት በሽታ መከላከል አቅም መዳከም

Bru-nO / Pixabay

ብቸኝነት የሰውነትን በሽታ መከላከል አቅም ያዳክማል። የዚህ ሁኔታ ምክንያት ተብሎ የሚገመተው ሰውነት በብቸኝነት ግዜ የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች ናቸው። ብቸኝነት እና ጭንቀት የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን የሚያወርዱ ሆርሞኖች እንዲመነጭ ያደርጋሉ።

2) ደም ግፊት

geraldoswald62 / Pixabay

ለአመታት ብቸኛ ሁነው ያሳለፉ ሰዎች ለደም ግፊት መጨመር ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ይህንን ሁኔታ የሚያጠኑ ሳይንቲስቶች ብቸኝነት የደም ግፊት መጨመር መንስኤ መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ባይችሉም ከፍተኛ ጥርጣሬ አላቸው።

3) አካል ብቃት እንቅስቃሴ

MartinKwame / Pixabay

ብቸኛ ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አባዜአቸው ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር የወረደ ነው። ከጓደኛ ጋር ዎክ ያድርጉ ወይም ጂም ይመዝገቡ። አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር የጭንቀት ስሜትን ከመቀነሱ በተጨማሪ አዲስ ሰው ለመተዋወቅ ጥሩ እድል ይፈጥራል።

4) የአእምሮ ፍጥነት

jarmoluk / Pixabay

ብቸኝነት የአእምሮ ፍጥነትን ሊያቀዘቅዝ ይችላል። ችግሮችን የመፍታት እና ነገሮች የማስታወስ ችሎታዎ ሊጎዳ ይችላል። እንደ አልዛይመር አይነት በሽታ የመጠቃት እድልዎንም ከፍ ያደርጋል። ለነዚህ አእምሮ ችግሮች ተጋላጭ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉ። ብቸኝነት ብቻውን አያመጣቸውም። ቢሆንም አንዱ የተጋላጭነት መንስኤ እንደመሆኑ ብቸኝነትን በመቀነስ ለአእምሮ ህምሞች ተጋላጭነታችንን መቀነስ እንችላለን።

5) ማጨስ

Tarabiscuite / Pixabay

ብቸኛ ሰዎች ብዙ ግዜ የማጨስ ሱስ ውስጥ ይገባሉ። ማጨስ ለእያንዳንዱ የሰውነት አካል መጥፎ ነው። የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታ እና የሳንባ በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል። ብዙ ሰዎች ጭንቀት ስሜት ሲሰማቸው ሲጋራ ይለኩሳሉ። ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከሆኑ ማቆም የሚችሉባቸውን መንገዶች ከዶክተር ጋር ይመካከሩ።

6) የልብ በሽታ

geralt / Pixabay

ለረጅም ግዜ የቆየ ብቸኝነት ለልብ በሽታ ተጋላጭ ያደርግዎታል። ከፍተኛ የሰውነት ክብደት፣ ከፍተኛ የደም ግፊት እና ከፍተና የኮሌስትሮል መጠን ተያያዥ ችግሮች ናቸው።

7) ድብርት(Depression)

Free-Photos / Pixabay

ድብርት ጤናን ያውካል። ብቸኝነት ድብርትን ያስከትላል። ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆይ የድብርት ስሜት ከተሰማዎ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የድካም ስሜት፣ የእንቅልፍ ችግር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ካጋጠመዎ ዶክተር ያማክሩ።

8) ክብደት መጨመር

jarmoluk / Pixabay

ብቸኝነት ለሰውነት ክብደት መጨመር ተጋላጭ ያደርገናል። ብቸኝነት ስሜትን ለማስታገስ ብለው የሚበሉት ምግብ መጠን ሊጨምር ይችላል። አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሊቀንሱም ይችላሉ። የስኳር በሽታ፣ የከፍተኛ ደም ግፊት እና ልብ በሽታ ተጋላጭነትዎ ይጨምራል። የሰውነት ክብደትዎ ከጨመረ ከሚበሉት ምግብ በተጨማሪ ስሜትዎን መከታተል ይጀምሩ።

9) እንቅልፍ

Sleep

ብቸኝነት እንቅልፍ ለመተኛት እንዲቸገሩ ምክንያት ይሆናል። ይህም በቀን በሚሰሩት ነገር ላይ በቂ ትኩረት እንዳይሰጡ ያደርጋል። እንቅልፍ እጦት ለጤንነትም ጠንቅ ነው። እንቅልፍ እጦት ከግዜ በኋላ ለስኳር በሽታ፣ ለከፍተኛ ደም ግፊት፣ ለልብ በሽታ፣ ለድብርት እና ለሰውነት ክብደት መጨመር ተጋላጭ ያደርገናል።

10) አልኮል እና እጾች

jarmoluk / Pixabay

ብቸኛ ሰዎች ብዙ አልኮል የመጠጣት እና አደንዛዥ እጽ የመጠቀም እድላቸው ከፍ ያለ ነው። እነዚህ ነገሮች ለግዜው የስሜት ፋታ ቢሰጡም ዘላቂ መፍትሄ አይደሉም። ከግዜ በኋላ ጤናችንን ማወክ ይጀምራሉ።

ብቸኝነትን ለመቀነስ ከሰው ጋር የሚቀራረቡበትን ግዜ ለመፍጠር ይሞክሩ። ቼዝ አብሮ መጫወት፣ የመጸሃፍ ክበብ መቀላቀል፣ ጂም መጀመር ወዘተ ከሰው ጋር ይበልጥ እንዲተዋወቁ ያደርጋሉ። እራስዎን ይንከባከቡ። አካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር፣ በግዜ መተኛት እና ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ የብቸኝነትን ስሜት ይቀንሳሉ።

ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ የብቸኝነት ስሜት ይሰማዋል። ነገር ግን በራስዎ የብቸኝነትን ስሜት ማጥፋት ካልቻሉ ዶክተር ያማክሩ። የስነ-ልቦና ምክር መውሰድ ዘላቂ ለውጥ እንዲያመጡ ሊረዳዎ ይችላል። የድብርት ስሜት የሚያስታግሱ መድሃኒቶችም ሊረዱዎት ይችላሉ።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ