ጤነኛ

ለረጅም እና ደስተኛ ጋብቻ ቁልፉ ምንድን ነው?

ሲያትል ከተማ ውስጥ የሚገኘው ጎትማን ኢንስቲቲውት( The Gottman Institute) ባካሄደው ጥናት እንደሚናገረው የረጅም ጋብቻ ሚስጥር ሁለቱም ባለትዳሮች ለትዳር አጋራቸው የሚያሳዩት ደግነት እና የስሜት እንክብካቤ ናቸው። አጋርዎን በሃሳብ ለመርዳት ይሞክራሉ ወይስ ለመተቸት እና ለመንቀፍ ቅርብ ነዎት? የአጋርዎን ጥሩ ጎን ነው የሚያዩት? የህይወት አጋርዎን ደስታ መጨመር ይፈልጋሉ? ደስተኛ ትዳር በቀን ውስጥ በትናንሽ ንግግሮች እና የጥሩ ሃሳብ ልውውጦች የተሞላ ነው።

jeremywongweddings / Pixabay

በባለ ትዳሮች መሃከል ያለ የምስጋና ስሜት ሌላ የጥሩ ትዳር ቁልፍ እንደሆነ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ጆርጂያ የተካሄደ ሌላ ጥናት ይናገራል። በትዳር አጋራቸው የሚመሰገኑ እና የሚሞገሱ ሰዎች ለትዳራቸው ይበልጥ ታማኞች እና ለህይወት መልካም አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው።

ሌላው የጥሩ ትዳር ሚስጥር ውሳኔዎችን በጋራ ማድረግ እና የቤት ውስጥ ስራዎችን ተከፋፍሎ ማከናወን ናቸው። ይህ እውነታ በጆርናል ኦፍ ፋምሊ ኢሹስ(Journal of Family Issues) መጽሄት በወጣ ጥናት ተረጋግጧል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ