ጤነኛ

አዲስ ወላጆች አብዝተው የሚፈጽሟቸው 10 ስህተቶች

ልጅ ወልዶ ማሳደግ መጀመር አስጨናቂ ነገር ነው። ስህተት እሰራለሁ ብሎ መጨነቅ አለ። እውነትም ነው። ሁሉም ወላጅ ሲጀምር ስህተት ይሰራል። ነገር ግን አዲስ ወላጆች በተደጋጋሚ የሚሰሯቸውን ስህተቶች አስቀድመን በማወቅ ስህተቶቻችንን መቀነስ እንችላለን። የሚከተሉት ነጥቦች አዲስ ወላጆች አዘውትረው የሚሰሯቸውን ስህተቶች እና ከስህተቶቹ እንዴት መቆጠብ እንደሚቻል ይዳስሳሉ።

ስህተት 1) በሁሉም ነገር መጨነቅ

StockSnap / Pixabay

ብዙ አዲስ ወላጆች ልጃቸው በሚያደርገው የተለመደ ተግባር ሁላ ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ። ምግብ ማስወጣት፣ ማልቀስም ሆነ የሆድ ጩኸት የተለመዱ ነገሮች ናቸው። ልጄ ተርቧል ወይስ ከመጠን በላይ በልቷል፣ በቂ ሰገራ እያስወጣ አይደለም፣ ምግብ እየከለከለው ነው፣ ብዙ እያለቀሰ ነው እያሉ ብዙ አዲስ ወላጆች ይጨነቃሉ። ነገር ግን ህጻኖች ከምናስበው በላይ ጠንካራ እና የሚፈልጉትን ነገር አዋቂ ናቸው። አንድ ችግር ካልተደጋገመ በስተቀር ብዙ ጭንቀት ውስጥ መግባት አያስፈልግም።

ስህተት 2) ልጅ እንዳያለቅስ ማጨናነቅ

grisguerra / Pixabay

ልጅ ማልቀስ ሲጀምር የትኛውም ወላጅ ለማባበል መሞከሩ ተገቢ ነው። ልጅ ሲያለቅስ የሆነ ማስተካከል ያለብን ችግር እንዳለ ይሰማናል። ነገር ግን ማልቀስ የህጻን ልጅ ባህሪ ነው። ልጅ ምንም የጤና ችግር ሳይኖርበትም፣ ሳይራብም፣ እራሱም ላይ ሳይጸዳዳም፣ በቂ እረፍት እንኳ አግኝቶ ያለቅሳል። በዚህ ሁኔታ አልቅሶ እስኪያቆም መተው ተገቢ ነው። ነገር ግን አንድ ህጻን ልጅ ከአንድ ሰአት በላይ ካለቀሰ ወይም የትኩሳት፣ የሽፍታ እና ማስመለስ ምልክቶች አብረው ከታዩበት ዶክተር ጋር መሄድ ተገቢ ነው።

ስህተት 3) ለማጥባት ከእንቅልፍ መቀስቀስ

gdakaska / Pixabay

ጡት ለማጥባት ልጅን ከእንቅልፍ መቀስቀስ አያስፈልግም። ልጅ ሙሉ ሌሊት እንቅልፍ ከወሰደው ለእናትም አብሮ መተኛት አስፈላጊ ነው። ጧት ሲነቃ ማጥባት ይቻላል።

ስህተት 4) ምግብ ማስወጣትን ከማስመለስ ጋር ማመሳሰል

በምግብ ማስወጣት እና ማስመለስ መሃከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢ ነው። ህጻን ልጅ አዘውትሮ ምግብ በቀላሉ ሊያስወጣ ይችላል። ብዙ ግዜ የማግሳትን ያህል በቀላሉ ምግብ ያስወጣል። ይህ ሁኔታ ሊያስጨንቅ አይገባም። ማስመለስ ግን ሃይል የተቀላቀለበት ባህሪ ነው። ተደጋጋሚም ነው። ልጁን የሆድ ቫይረስ ካጠቃው በየ30 ወይም 40 ደቂቃው ሊያስመልሰው ይችላል። በዚህ ግዜ ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።

ስህተት 5) ትኩሳትን ችላ ማለት

congerdesign / Pixabay

ህጻኑ ልጅ 3ወር ሳይሞላው ከ100ዲግሪ በላይ ትኩሳት ከተነሳበት ለጤናው አደጋ ስለሆነ ዶክተር ጋር መውሰድ ያስፈልጋል። የህጻን ልጆች ሰውነት በሽታ መከላከል አቅሙ እስኪዳብር ግዜ ይወስዳል። በዚህ ግዜ ውስጥ ልጁ ከፍተኛ ትኩሳት ካለው ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።

ስህተት 6) መኪና ውስጥ በአግባቡ አለማስቀመጥ

Tammydz / Pixabay

ልጅ መኪና ውስጥ ካለ በሰው እቅፍ ውስጥ መሆን አለበት ወይም የህጻን ልጅ ወንበር መኪና ውስጥ ተገጥሞ በሱ መታቀፍ አለበት። ልጅን ጀርባ ወንበር ላይ አስቀምጦ መንዳት ልጁን አደጋ ውስጥ ይከታል።

ስህተት 7) የልጁን የአፍ እና ጥርስ ጤና ችላ ማለት

collusor / Pixabay

ጥርስን ማጽዳት ለህጻን ልጆችም አስፈላጊ ነገር ነው። የልጅን ጥርስ ጤና ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሏቸው የተወሰኑ ነገሮች አሉ። ልጅ ጥርስ ማብቀል ከጀመረ በተኛበት ጡት መስጠት ተገቢ አይደለም። በተኛበት ማጥባት የጥርስ መቦርቦር እድሉን ከፍ ያደርጋል። ልጅ አንድ አመት ከሞላው በለስላሳ ጥርስ ብሩሽ መፋቅ መጀመር ይችላል። ፍሎራይድ በውስጡ የያዘ የጥርስ ሳሙና ለጥርስ ጤና ተስማሚ ነው።

ስህተት 8) በልጅ ምክንያት ትዳርን ችላ ማለት

jeremywongweddings / Pixabay

ለልጅ እንክብካቤ ሲሰጡ የትዳር አጋርዎን መርሳት የለብዎትም። ብዙ አዲስ ወላጆች ትኩረታቸውን ወደ ልጅ በሚያደርጉበት ግዜ የትዳር አጋራቸውን ችላ ማለት ይጀምራሉ። ጤነኛ ትዳር ለእርስዎም ሆነ ለልጅዎ ዘላቂ ደስታ በጣም አስፈላጊ ነው።

ስህተት 9) በልጁ ፊት ከባለቤትዎ ጋር አብዝቶ መጋጨት

Josethestoryteller / Pixabay

ልጅ በህጻንነቱ እንኳ በሰዎች መሃከል ያለውን መጥፎ ስሜት መረዳት ይችላል። ከባለቤትዎ ጋር በህጻን ፊት መጋጨት የልጅን ስሜት ይረብሻል። በባለቤትዎ ሲበሳጩ እንኳ በልጅ ፊት ማክረር የለብዎትም።

ስህተት 10) ልጅ የማሳደግ ምክር ከማይሆኑ ቦታዎች መውሰድ

stokpic / Pixabay

ኢንተርኔት ወላጆች ስለ አስተዳደግ ብዙ መረጃ የሚያገኙበት መስኮት ነው። ነገር ግን ስለ ልጅ አስተዳደግ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት ይሚያነቡበት ዌብሳይት የሚታመን መሆኑን አስቀድመው ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ