ጤነኛ

ወንድ እና ሴት በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ከሚፈልጓቸው ነገሮች 8 ልዩነቶች።

ወንድ እና ሴት በአካል እንደሚለያዩ ለማንም ግልጽ ነው። በስሜት ግን እንዴት እንደምንለያይ ብዙ ሰው አያውቅም። አልጋ ውስጥ የተሻለ ግንኙነት እንዲኖረን የስሜታዊ ልዩነቶቻችንን ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል።

መጀመርያ ሴቶች ከሚፈልጓቸው ነገሮች እንነሳ።

1) ምድጃውን ማሞቅ አለብህ

ሴት ልጅ ግንኙነትን ለማጣጣም ሮማንቲክ ነገር እንዲደረግላት ትፈልጋለች። ስጦታ መስጠት፣ እሷን ማዳመጥ አንተን እንድትታመን የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው። አበባም ይሁን ጥሩ የእራት ግብዣ እሷ ላንተ የተለየች እንደሆነች የምትነግርባቸው ነገሮች ናቸው።

2) ሩጫ አይደለም

3194556 / Pixabay

ግንኙነት ከመጀመርህ በፊት ግዜ ወስዶ መሳሳም፣ መተቃቀፍ እና መተሻሸት ያስፈልጋል። ሴቶች ስሜት ውስጥ ለመግባት ከግንኙነት በፊት ቢያንስ ለ20 ደቂቃ አካላዊ ንክኪ፣ መሳሳም ይፈልጋሉ። ላንተ ረጅም ደቂቃ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በመነካካት ሰውነታችሁን የምትተዋወቁበት ግዜ ለሷ ስሜት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።

3) ግንኙነት ወቅት ነገሮችን መቀያየር ያስፈልጋል

macadam13 / Pixabay

ግንኙነት እንደስፖርት ነው። ሁሌ ተመሳሳይ ነገር ሲሆን ለሱ ያለን ፍላጎት ይቀንሳል። ትላንት ያደረከው ነገር ስሜት ጣራ ላይ አደረሳት ማለት ዛሬም ነገም ሲደገም ይሰራል ማለት አይደለም። የተለያዩ የግንኙነት ፖሲሽኖችን መሞከር አለብህ። የግንኙነት ፍላጎቶቻችሁን እያወራቹህ አውቃቹህ እርስ በእርስ የሚያስደታችሁን ነገር ማድረግ አስፈላጊ ነው። በንግግር ወቅት ግን የሷን የግንኙነት ጥያቄዎች ማንቋሸሽ ወይም ማሳነስ በፍጹም የለብህም።

4) እሷን ሁሌ የስሜት ጣርያ ማድረስ የለብህም

ብዙ ወንዶች ሴቷን የስሜት ጣርያ ላይ ማድረስን ብቻ ነው እንደ ስኬት ምልክት ይሚያዩት። አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ለስኬት ብቸኛ መለክያ መሆን የለበትም።

አንዳንዴ ሴቶች ስሜት ጣርያ ሳይደርሱ እንኳ በግንኙነት ደስተኛ የሚሆኑበት ግዜ አለ። በግንኙነት ወቅት ካነተ ጋር የሚሰማትን የስሜት ውህደት ወይም አንተን ስሜት ጫፍ ስተደርስ ማየት ለሷ ደስታ ይሆናል።

አንዳንድ ቀን ስሜት ጣርያ መድረስ ትፈልጋለች። አንዳንዴ ደግሞ ግንኙነቱ የሚሰጣትን ስሜት ማጣጣም የምትፈልግበት ግዜ ይኖራል። ስሜት ጣርያ አላደረስኳትም ብለህ እንደሽንፈት ማየት የለብህም።

በአጠቃላይ ሴቶች የወንድን ያህል ግንኙነትን ይፈልጉታል። ስሜት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ግን መጀምርያ ሮማንስ አና ፍቅር ይፈልጋሉ።

ወንዶች የሚፈልጓቸው ነገሮች

1) አቅጣጫ መስጠት

ወንድ አንቺን ያስደሰተሽ ነገር ካገኘ እሱን መደጋገሙ አይቀርም። ነገሮችን ቀየር እንዲሉልሽ ከፈልግሽ ወይም ስሜትሽን የሚጨምር ነገር እንዲያደርግ ከፈልግሽ ግንኙነት ላይ አቅጣጫ መስጠት ትችያለሽ።

የምትፈልጊው ቦታ ሲሄድ የማቃሰት ድምጽ በማሰማት የምትፈልጊው ቦታ በቀላሉ እንዲደርስ ማድረግ ትችያለሽ። ለሱም ኮንፊደንስ ትሰጪዋለሽ። እጁንም እየወስድሽ እንዲነካሽ የምትፈልጊው ቦታ መውሰድ ትችያለሽ።

2) ሁሌ ግንኙነት ይፈልጋል

ወንድ ልጅ ስሜት ውስጥ ለመግባት ቅጽበት ይበቃዋል። እንቺ ግዜ ይፈጅብሻል። አንዳንዴ ለሱ ደስታ መስጠት ካሰብሽ ቶሎ ግዜ ሳትፈጂ ለሱ ግንኙነት መስጠት ልዩ ስሜት ሊሰጠው ይችላል።

የፍጥነት ግንኙነት ወይም ቁዊኪ ለሱ ልትሰጪው የምትችዪ ስጦታ ነው። በኋላ ደግሞ እሱ በደንብ ግዜ ወስዶ ግንኙነት እንዲያደርግሽ ማበረታቻ ይሆናል።

3) ንግግርን ከአልጋ ውጪ ማድረግ ተገቢ ነው

አንዳንዴ አቅጣጫ መስጠት በቂ ላይሆን ይችላል። እሱ የግንኙነት መንገዱን እንዲቀይር ማነጋገር ካለብሽ በግንኙነት ወቅት መሆን የለበትም። ግንኙነት ግዜ የሁለታችሁም ስሜት የተጋለጠበት ግዜ ነው። በዛ ወቅት ስሜቱን ሊጎዳ ይሚችል ንግግር ማድረግ አስፈልጊ አይደለም። ከግንኙነት ውጪ የሚደረግ የግንኙነት ንግግር እንደ ፍቅረኛ ይበልጥ ሊያቀራርባቹህ ይችላል።

4) መግፋት ይበልጥ ያርቀዋል

Jonesee / Pixabay

እሱ ግንኙነት ማድረግ ፈልጎ አንቺ ስላልፈልግሽ አልፈልግም ብሎ መተው እሱን ካንቺ ሊያርቅ ይችላል። ወንድ አንቺን ለመቅረብ፣ ስሜቱን ለማጋለጥ ግንኙነት ያስፈልገዋል። ግንኙነት አልፈልግም ማለትሽ ያን ሁሉ ነገር አልፈልግም እንዳልሽ አድርጎ ይቆጥረዋል። በየግዜው እንደማትፈልጊ ከነገርሽው ላንቺ ያለውን የግንኙነት ፍላጎት እያጣ ይመጣል። ይርቅሻል።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ