ጤነኛ

ፍቅር ግንኙነትዎን የሚጎዱ 10 ልማዶች ከነመፍትሄያቸው

በፍቅር ግንኙነት ውስጥ በቆዩ ቁጥር ግንኙነቱ ጠንካራ እና የተረጋጋ እየሆነ ይመጣል። እውነተኛ ማንነትዎ በደንብ መታየት ይጀምራል። እንደዛ መሆን ለግንኙነታቹህ አስፈላጊ ቢሆንም ሲመቻቹ የሚያሳዩዋቸው ባህሪያት ግንኙነትዎን ሊጎዱ ይችላሉ።

በየትኛውም ግንኙነት ውስጥ አልፎ አልፎ አለመስማማት የተለመደ ቢሆንም ፍቅርዎን የሚሸረሽሩ ተደጋጋሚ ልማዶችን ተገንዝቦ ማስተካከል አስፈላጊ ነው። ለራሳችን የሚታወቁን ሆነም የማይታወቁንን መጥፎ ልማዶች ተረድተን በማስተካከል ጓደኛችንን ከማራቅ መታደግ አለብን።

11 ግንኙነት የሚረብሹ ተደጋጋሚ ልማዶች ከነመፍትሄዎቻቸው እነሆ፡

1) የፈጠሩትን ቆሻሻ አለማጽዳት

Hans / Pixabay

የፈጠሩትን ቆሻሻ አለማጽዳት ፍቅረኛዎትን መረበሹ አይቀርም። በተለይ እሱ ወይም እሷ የጽዱ ልማድ ካላቸው። በቤትዎ ያልታጠበ ልብስ ክምር፣ ሲንክ ላይ ያልታጠቡ እቃዎች፣ ያልተጸዳ ቆሻሻ ክምር ጽዱ ያልሆነ ሰው መገለጫ ናቸው። አብራችሁ ብትኖሩም ተለያይታቹህ ጽዱ ቤትዎን በጽዱ ሁኔታ መያዝ ለግንኙነታቹህ አስፈላጊ ነው። ፍቅረኛዎን ቤት አጽጂዎ ማድረግ ግንኙነትዎን ይጎዳል እንጂ አይጠቅመውም።

መፍትሄ
ልምድዎን ቀስ በቀስ ማሻሻል መጀመር አለብዎ። ለምሳሌ ልብስዎ ቆሽሾ ሲከማች ከማየት በሳምንቱ አንዱን ቀን ልብስ የማጠብያ ቀን አድርገው ካስፈለገ አላርም ሞልተው ማጽዳት አለብዎ። ቤትዎን ለማጽዳትም ሆነ ቆሻሻዎን አውጥቶ ለመጣል ተመሳሳይ መላ መጠቀም ይችላሉ።

እንደ እቃ ማጠብ እንደመሳሰሉት ቀን በቀን መሰራት ላለባቸው ነገሮች ከሰሩት በኋላ የሚቀልዎትን ስሜት እያስታወሱ እራስዎን ማበረታታት ይችላሉ። አብረው የሚኖሩ ከሆነ ቤት ውስጥ ያለውን ስራ ተነጋግራቹህ መከፋፈል ጥሩ ነው። አንዳቹህ ላይ ሁሉም ስራ ከተጣለ ለግንኙነታቹህ መሻከር ምክንያት ይሆናል።

2) ንዝንዝ

OpenClipart-Vectors / Pixabay

ፍቅረኛዎን በተመሳሳይ ጉዳይ መነዝነዝ ግንኙነትዎን የሚረብሽ ዋነኛ ነገር ነው። ፍቅረኛዎን አንድ ነገር ጠይቀው ባለማድረጉ ወይም ባለማድረጓ መበሳጨት የተለመደ ነው። ነገር ግን ሁልግዜ እሱን እያነሱ መጨቃጨቅ መፍትሄ አይደለም። ፍቅረኛዎን ከእርስዎ የበለጠ ያርቃል።

መፍትሄ፡
በፍቅረኛዎ ላይ ንዴት ሲሰማዎ ወደኋላ መለስ ብለው ግዜ እንዲያልፍ አድርገው ስሜቱ ሲያልፍ በተረጋጋ ሁኔታ መነጋገር አስፈላጊ ነው። ከፍቅረኛዎ የሚፈልጉትን ነገር ቁጭ አድርገው በመነጋገር ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው። “አንተ ሁሌም አርፋጅ ነህ” ወይም “አንቺ ቤት ማጽዳት አይሆንልሽም” በማለት የሚነሱ ክሶች ነገሮችን ያጋግላሉ እንጂ አይፈቱም። አነጋገርዎን ወደ ጥያቄ በመቀየር ፍላጎትዎን ግልጽ ማድረግ ይችላሉ። “በግዜ መምጣት ልማድ እንዲሆንህ እፈልጋለሁ” እና “እንዳንዴ ቤቱን ብታጸጂው ደስተኛ እሆናለሁ” በማለት አነጋገራችንን ቀይረን መልእክታችንን ማድረስ እንችላለን። ትእዛዝ እና የቁጣ ንግግር ከበለጠ ንዴት እና መቀያየም የዘለለ ፍጻሜ የላቸውም።

3) ፍቅረኛ ላይ ተንጠልጣይ መሆን

ሁሌም ፍቅረኛዎ አብሮዎት እንዲሆን/እንድትሆን መፈለግ፣ ያለማቋረጥ ፍቅረኛዎ ጋር መደወል፣ ፍቅረኛው ከእርስዎ ውጪ ባለው ግንኙነቶች ባለመካተትዎ ማዘን፣ ስልክ መልሶ ባለመደወሉ በሜሴጅ ማጨናነቅ የተንጠልጣይ ምልክቶች ናቸው። በፍቅር ምክንያት ቢሆንም የሚያደርጉት እነዚህ ባህሪያት ፍቅረኛዎን ያርቃሉ እንጂ አያቀርቡትም።

መፍትሄ፡
በራስዎ መተማመን መጀመር አለብዎ። እራስዎን መውደድ እና ከፍቅር ግንኙነትዎ ውጪ ሌሎች ግኑኘንቶችን፣ ማዳበር አለብዎ። ለጥሩ ግንኙነት በመሃላቹህ የተወሰነ ክፍተት ሊኖር ይገባል።

4) የፍቅረኛዎን ግላዊ ነገሮች አለማክበር

PublicDomainPictures / Pixabay

ፍቅረኛዎ የሚጻጻፋቸውን እና የሚደዋወላቸውን እሱ/እሷ በሌሉበት ማየት በመሃከላቹህ የሚያስፈልገውን መተማመን የሚያጠፋ ነገር ነው። መልእክት አይተው ማረጋገጥ ቀላል መንገድ ቢመስልም በሚታወቅ ግዜ የፍቅረኛዎን ግላዊንት ባለማክበርዎ ወደ ጥል ያመራሉ።

መፍትሄው፡
የመከታተሉ ስሜት ሲሰማዎት መፍትሄ እንዳልሆነ እራስዎን ማስታወስ አለብዎ። የመጠራጠር ስሜቱ የመጣው በፍቅረኛዎ ባህሪ ከሆነ በግልጽ መነጋገር ያስፈልጋል። በእርስዎ ፍራቻ ከሆነ ግን ስሜቱን ተገንዝበው ማለፍ አለብዎ። ፍቅረኛዎ እርስዎ እንደሚከታተሉት እሱ/እሷ ቢከታተልዎ እንዴት እንደሚሰማዎ ማሰብ ይኖርብዎታል።

5) ከልክ ያለፈ መተራረብ

በሚያስደስት ቀለል ካለ መቀላለድ እና ስሜት ያልጠበቀ ዝልፊያ መሃከል መስመር አለ። እርስ በእርስ መቀላለድ የግንኙነታችሁን ጤነኛነት ያሳያል። ነገር ግን ማሸነፍ አለብኝ በሚል ስሜት የሚጎዳ ንግግር ከማድረግ መቆጠብ ያስፈልጋል። በተለይ ፍቅረኛዎ በሚያፍሩበት በሚሸማቀቁበት ነገር መቀለድ ለጥል ይዳርጋል።

መፍትሄ፡
የፍቅረኛዎን ስሜት ጫፍ ማወቅ አለብዎ። በፍቅረኛዎ ድክመት መቀለድ የለብዎትም። የፍቅረኛዎን ድክመት ክብር በተቀላቀለበት ንግግር የሚፈቱት ነገር እንጂ ፌዝ የሚያፌዙበት ነገር አይደለም።

6) እራስዎን አለመንከባከብ

Leroy_Skalstad / Pixabay

የራስዎን ሰውነት እና ጤና አለመጠበቅ ፍቅረኛዎን ከሚያረቁ ወነኛ መክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው። ስፖርት በመስራት አካልዎን መጠበቅ፣ ህመም ካለብዎ ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣ አለማጨስ፣ ብዙ አለመጠጣት፣ በስራ ከሚገባው በላይ አለመጠመድ ፍቅረኛዎ ከእርሶ የሚጠብቁት ነገሮች ናቸው።

መፍትሄ፡
ልምድዎትን በደንብ መከታተል አለብዎ። እራስዎንና እና ሰውነትዎን እንዴት እየተንከባከቡት እንደሆነ ቆም ብለው ማየት አለብዎ። ስፖርት ለመስራት የሚያደክም ቀን የሚያሳልፉ ከሆነ ሰውነትዎ የሚንቀሳቀስበት እንደ ዎክ ማድረግ ወይም በቤትዎ ቀላል ስፖርት የሚሰሩበት ሁኔታ መፍጠር ተገቢ ነው።

7) ሁሌ ፍቅረኛዎ ግብረስጋ ግንኙነት እስኪጀምር መጠበቅ

ግንኙነትም ሆነ መሳምን ወይም መተቃቀፍን ሁሌ ፍቅረኛዎ እንዲጀምር መጠበቅ የልብዎትም። እሱ ወይም እሷ እስኪጀምር ሁሌ የሚጠብቁ ከሆነ ፍቅረኛዎ ለእሳቸው ያለዎት ስሜት የቀዘቀዘ እንደሆነ ነው የሚያስቡት። ግንኙነት ሸክም የሆነብዎት ነው የሚመስላቸው። በደስታ መፈጸም አይችሉም።

መፍትሄ፡
በየቀኑ ለፍቅረኛዎ የፍቅር ስሜት መግለጽ እንዳለብዎ ያስታውሱ። ለምሳሌ ሲገናኙ ፍቅርኛዎን በማቀፍ ሰላም ይበሉ። አብረው ሲራመዱ እጃቸውን ይያዙ። ሲሰናበቱ ተሳሳሙ። ስሜትዎ ከተቀሰቀሰ ግብረስጋ ግንኙነት ለመጀመር ወደኋላ አይበሉ። በግንኙነትዎ ተሳፋሪ አይሁኑ።


8) ፍቅረኛዎን በተደጋጋሚ መተቸት። ለመቀየር መሞከር።

27707 / Pixabay

ፍቅረኛዎን ለመቀየር መሞከር የመለያየት እና ፍቺ ቀዳሚ ምክንያት ነው። የልማድ ለውጦችን መጠየቅ የተለመደ ቢሆንም የፍቅረኛዎን ማንነት ለመቀየር መሞከር መጨረሻው ጥል ነው። ሰው መቀየር የማይችላቸው እና ተገቢ ቅያሬ ያልሆኑ ነገሮች አሉ። የፍቅረኛዎን ማንነት ተረድተው ከእርስዎ ጋር እንደሚጣጣሙ ነው መረዳት ያለብዎ።

መፍትሄ፡
የፍቅረኛዎን ጸባይ መቀበል ለጥሩ ግንኙነት አስፈላጊ ነው። ፍቅርዎን አጠንክሮ ለማቆየት የፍቅረኛዎን በጎ ባህሪዎች ላይ ያተኩሩ። ከልክ ያለፈ ነገር ከፍቅረኛዎ አይጠብቁ። በማንነታቸው ተቀብለው ፍቅር ይስጡዋቸው።

9) ቴክኖሎጂ ጋር ብዙ ሰአት ማጥፋት

philpace / Pixabay

ስልክዎ፣ ኮምፒውተርዎ እና ቲቪ ላይ ረጅም ሰአት ተጥደው የሚቆዩ ከሆነ የፍቅረኛዎን ሰአት እየተሻሙ ነው ያሉት።

መፍትሄ፡
ቴክኖሎጂ አጠቃቀምዎ ላይ የሚከተሉት ህግ ያስቀምጡ። ከፍቅረኛዎ ጋር ግዜ እያሳለፉ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር አይጠቀሙ።

10) ፍቅረኛዎን መቆጣጠር መሞከር

ሁሉንም ውሳኔ እርስዎ ከሆነ የሚያደርጉት ከልክ በላይ ተቆጣጣሪ እንደሆኑ መረዳት አለብዎ። ምን እንደምትበሉ፣ ምን እንደምታዩ፣ ከማን ጋር እንደምትገናኙ፣ ገንዘብ ምን ላይ እንደምታውሉ ሁሌ የሚወስኑት እርስዎ ከሆነ ግንኙነትዎን አደጋ ላይ ይጥላሉ። ግንኙነቶች በትብብር እና በመቻቻል ስሜት ካልቀጠሉ ግንኙነቱ ይጎዳል።

መፍትሄ፡

የመቆጣጠር ስሜት አብዛኛው ግዜ ከፍራቻ የሚመጣ ነው። ፍቅረኛዎን መቆጣጠር ከሞመከር የራስዎን ፍራቻ ነው ማስታገስ ያለብዎ። የራስዎን ስሜት የመከታተል ልምድ ይኑርዎ። ውሳኔ ከመውሰድዎ በፊት ቆም ይበሉና እድሉን ለፍቅረኛዎ አሳልፈው ይስጡ።

ማንኛውም ልምድ ለመቀየር ከባድ ነው። ግዜ፣ ጥረት እና ትእግስት ያስፈልጋል። ከሞከሩ ግን መቀየር በቁጥጥርዎ ስር ያለ ነገር ነው።

Tenegna

አነጋግሩን

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። እባክዎ አነጋግሩን።

በጣም የታዩ